ወግ አጥባቂዎቹ አስተማማኝ ድምፅ አግኝተዋል | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 27.09.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

ወግ አጥባቂዎቹ አስተማማኝ ድምፅ አግኝተዋል

ሽታይማየር የሚወክሉት የሶሻል ዲሞክራቶቹ ፓርቲ SPD መጀመሪያ ከተገመተዉም ቁልቁል ወርዶ 148 መቀመጫዎች አግኝቷል

default

የCDU/CSU ደጋፊዎች ፌስታ

በጀርመን አቆጣጠር እኩለ ሌሊት ግድም ይፋ በሆነዉ ዉጤት መሠረት፥ ወግ አጥባቂዉ የአንጌላ ሜርክል እሕትማማች ፓርቲ CDU/CSU ካጠቃላዩ የምክር ቤት መቀመጫ 238ቱን በማሸነፍ-የአንደኝነቱን ሥፍራ ይዟል።ሽታይማየር የሚወክሉት የሶሻል ዲሞክራቶቹ ፓርቲ SPD መጀመሪያ ከተገመተዉም ቁልቁል ወርዶ 148 መቀመጫዎች አግኝቷል።የነፃ ዲሞክራቶቹ ፓርቲ FDP 93 መቀመጫዎችን አግኝቷል።የግራዎቹ ፓርቲ 76 አረንጓዴዎቹ ደግሞ 67 መቀመጫዎችን አሸንፈዋል።
ነጋሽ መሐመድ