ክፍል 34- የቤትሆፈን ቤት ክስተቶች | Radio D Teil 2 | DW | 09.11.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

Radio D Teil 2

ክፍል 34- የቤትሆፈን ቤት ክስተቶች

ፊሊፕ እና ፓውላ በቤትሆፈን ቤት ማታ ማታ ግሩም አድርጎ ፒያኖ የሚጫወተው ማን መሆኑን ለማወቅ ይፈልጋሉ። ሁለቱ ጋዜጠኞች ባቅራቢያው በሚገኝ አንድ ቡና ቤት ውስጥ አስገራሚ የሆኑ ሌሎች ነገሮችን ይሰማሉ። የሰሙት በርግጥ እውነት ነው ወይስ ጭምጭምታ ብቻ ነው?

ከአንድ አጭር ሌሊት በኋላ ፓውላ እና ፊሊፕ በቤትሆፈን ቤት አቅራቢያ በሚገኘው ቡና ቤት ቁጭ ብለው አጠገባቸው ከተቀመጡት ሶስት የሙዚቃ ትምህርት ከሚከታተሉ እንግዶች የሚገርም ንግግር ያደምጣሉ። ሌሊት ሌሊት ማን ፒያኖ እንደሚጫወት ተማሪዎቹ የሚገምቱት ነገር አለ። ፓውላ እና ፊሊፕ ስለ አንድ ከፍተኛ የሙዚቃ ተሰጥዖ ያለው እና ብዙዎች «ቤትሆፈን» ብለው ስለሚጠሩት ፒያኖ ተጫዋች ተማሪ ታሪክ ይሰማሉ።
ፓውላ እና ፊሊፕ በቤትሆፈን ቤት ውስጥ ስለዚሁ ፒያኖ ተጫዋች ማንነት የበለጠ ለማወቅ ሲጥሩ፣ ፕሮፌሰሩ ወቅታዊ ያልሆኑ ጥያቄያዊ ዓረፍተ ነገሮች እንዴት ያለ መጠይቅ ቃል እንደሚቀርቡ ይመራመራሉ።

Downloads