ኬንያና ስለ ሰብአዊ መብት ጩኸቱን ያሰማ የነበረ አንድ ዜጋዋ መሠወሩ፧ | አፍሪቃ | DW | 28.08.2007
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

ኬንያና ስለ ሰብአዊ መብት ጩኸቱን ያሰማ የነበረ አንድ ዜጋዋ መሠወሩ፧

ፋራህ ሙሐመድ አብዱላሂ የተባለ የኻያ ስድስት ዓመት ወጣት ኬንያዊ፧ በአሸባሪነት ተጠርጥረው፧ ከኬንያ ወደ ኢትዮጵያ የተሸጋገሩና የታሠሩ ሰዎች፧ መጀመሪያውንም ወደ ሌላ አገር መወሰድ አልነበረባቸውም በማለት

አሜሪካ፧ የሚፈለጉ ያለቻቸው በኧል ቓኢዳ አባልነት የተጠረጠሩ ሰዎች ፎቶግራፍ፧

አሜሪካ፧ የሚፈለጉ ያለቻቸው በኧል ቓኢዳ አባልነት የተጠረጠሩ ሰዎች ፎቶግራፍ፧

በአደባባይ ጩኸቱን ሲያሰማ ከቆየ በኋላ፧ ከ ዘጠኝ በፊት ናይሮቢ ውስጥ መሠወሩን፧ AP አስታውቋል። ሙሐመድ አብዱላሂ፧ ከመሥጊድ እንደተመለሰ፧ የሲቭል ልብስ በለበሱ ሥስት ሰዎች ተገዶ በመኪናቸው እንዲሣፈር ከተገደደ ወዲህ ድምፁ አለመሰማቱን አባቱ፧ ሙሐመድ አብዱላሂ አስታውቀዋል። ጉዳዩን Muslim Rights Forum የተባለው የኬንያ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት በመከታተል ላይ ሲሆን፧ ተክሌ የኋላ የድርጅቱን ሊቀመንበር፧ ኧል አሚን ኪማቲን በስልክ አነጋግሮአቸዋል።
«ከኬንያ ባለሥልጣናት በኩል ያን ያህል ፍንጭ ማግኘት አልተቻለም፧ ከፖሊስም ሆነ ከራሱ ከመንግሥት፧ ስለፋራህ ሙሐመድ አብዱላሂ ደብዛ የተገኘ ፍንጭ የለም። እኔና የአብዱላሂ ቤተሰብ የፖሊስ ጣቢያዎችን ሁሉ አሥሠናል፧ ማብራሪያም እንዲሠጠን ጠይቀናል። ግን፧ ከባለሥልጣናቱ በኩል የተሰጠ ማብራሪያ የለም። ስለዚህ ጥረታችንን በማጠናከር ፍርድ ቤት በዚህ ጉዳይ ላይ፧ ማለት አብዱላሂ ሳየለፍ አልቀረም ስለተባለበት ሁኔታ ማብራሪያ እንዲሰጥ ከቤተሰቡ ጋር ሆነን እንጠይቃለን። ነገ ጧት፧ ከኬንያ ፖሊስ አዛዥ ጋር ቀተሮ ይዘን ለመነጋገር ተስፋ አድርገናል።«
ፋራህ ሙሐመድ አብዱላሂ፧ ስለሰብአዊ መብት በአደባባይ ጩኸቱን በማሰማት ያደርግ በነበረው ትግል ድንገት የአገሪቱን ህግ የተላለፈበት ሁኔታ ነበረ ወይ?
«የወንድሙን መብትና ነጻነት አስመልክቶ ያደርግ በነበረው ትግል የሀገሩን የኬንያን ህግ የጣሰበት ሁኔታ የለም። በህገ-መንግሥት ያገኘውን መብት መሠረት አድርጎ ነበረ የሚንቀሣቀሠው። ህግ ይጥሳል ብለን አናምንምወንድሙ፧ ከዓመቱ መግቢያ አንስቶ(ካለፈው ጥር ወር ገደማ አንስቶ ማለታቸው ነው!) ህገ ወጥና ትክክለኛ ባልሆነ አሠራር፧ ክሥ ሳይመሠረትበት በእሥር ቤት በመማቀቅ ላይ ነው የሚገኘው። ወደ ኢትዮጵያ እንዲሸጋገር የተደረገውም በዚህ ባገሩ መንግሥት አማካኝነት ነው። ምናልባትም፧ ወንድሞ ተመልሶ ለኬንያ መንግሥት እንዲሠጥ ተደርጎ ይሆናል የሚባለውንም፧ በመመርመር ላይ ነን፧ ከእሥር ቤት የተለቀቁ አንዳንድ እሥረኞች የተባለው ሳይሆን እንዳልቀረ በመተቆማቸው! ያጋለጠው ጉዳይ ይኑር-አይኑር ከዚህ ሌላ የምናውቀው የለም። እርግጥ እንደሚመስለን፧ ወንድሙ እሥር ቤት ውስጥ ቢሆንም፧ የቅርብ ግንኙነት የነበረው በመሆኑ፧ ይህ ራሱ የኬንያን ፀረ-አሸባሪነት ኃይልም ሆነ ቡድን አስቆጥቶ ሊሆን ይችላል። ከወንድሙ ጋር ባደረገው ውይይትም፧ ዜናው ለዓለም እንዲዳረስና የሰብአዊ መብት ድርጅቶችም ኢትዮጵያ ውስጥ በእሥር ላይ የሚገኙት እንዲፈቱ ይጥሩ ዘንድ አግባብቶ ይሆናል።«
የፋራህ ሙሐመድ አብዱላሂ ወንድምም ሆነ ሌሎቹ በአሸባሪነት ተተርጥረው የተያዙት ሰዎች በአገረው ህግ እንደመዳኘት፧ ለምን ወደ ሌላ አገር ተወሰዱ? የአገሪቱ ህግ ይፈቅዳል ማለት ነው?
ይህ፧ ሁልጊዜ፧ ጥያቄአችን ሆኖ የቆየ ጉዳይ ነው። ማንኛውም ተጠርጣሪ ማንኛውንም ዓይነት ወንጀል ይፈጽም፧ ኬንያ ውስጥ ማለት ነው፧ የአገሪቱ ዜጋም ሆነ አልሆነ መዳኘት ያለበት በኬንያ ፍርድ ቤት ነው። በወንጀል የተጠረጠሩ ወደሌላ ሁለተኛ አገር ይዛወሩ ከተባለም ውሳኔው የኬንያ ፍርድ ቤት ጉዳይ ነው። በዚህ ርእሰ ጉዳይ ግን የሚገርመው አብዱላሂና ቀሪዎቹ የአገሪቱ ህግ እንደሚጠይቀውም ሆነ እንደሚያዘው ሳይሆን ከዚህ አንጻር ወደሌላ አገር እንዲዛወሩ ተደርጓል። ይህ የኬንያን ህግም ሆነ ህገ መንግሥት ሙሉ-በሙሉ የጣሰ እርምጃ ነው።«