ከጋምቤላ የታገቱትን ሕፃናት የመመለሱ ጉዳይ | ኢትዮጵያ | DW | 02.06.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ከጋምቤላ የታገቱትን ሕፃናት የመመለሱ ጉዳይ

ባሳለፍነዉ ወር በደቡብ ሱዳን የሚኖሩ የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ጋምቤላ ክልል ሰርገው በመግባት 208 ሰዎች ገድለው፣ ከ108 በላይ ሕፃናት እና ሴቶችን ማገታቸው ይታወሳል። ይህን ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግስት ጦር ሃይሉን በመላክ ጥቂቶቹን ያስለቀቀ ሲሆን የተቀሩትን ታጋቾች ወደ ሃገራቸው ለመመለስ በድርድር ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 02:23

ጋምቤላ

ከመጀመርያዉ ጀምሮ የኢትዮጵያ መንግስት ሃይል ከመጠቀም ይልቅ የታገቱትን ሕፃናት በድርድር እንድሚመለስ ከመናገር ወደ ኋላ አላለም። እስከ አሁን አንዴ በአስር አንዴ በሰላሳዎቹ ከስር ከስር ወደ 63 ሕፃናት እንዲመለሱ ተደርገዋል። ቀሪዎቹንም ታጋቾች መልሶ ለማምጣት ፍለጋዉ ተጠናክሮ እንደቀጠለ እና በሁለቱም ሃገራት መካካል የተደረገዉ ስምምነት ሕፃናቱን መልሶ ለማምጣት እንደሚያስችል የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ባሳለፍነዉ ዓርብ የክልሉን ፕሬዝዳንት አቶ ጋትላኡክ ቱትን ጠቅሶ ዘግቦታል።

የተመለሱት ሕፃናት ሁኔታን አስመልክተው የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃልአቀባይ አቶ ተወልደ ሙሉጌታ ለዶይቼ ቬሌ እንዳስታወቁት፣ ሕፃናቱን መመለስ የቻሉት በደቡብ ሱዳን ከሚገኙ ማህበረሰብ እና ከመንግስታቸዉ ጋር ባደረጉት ድርድር ነዉ። የኢትዮጵያ መንግስት ሕፃናቱን ለማስለቀቅ ከድርድሩ ዉጭ የተጠቀመበት ሌላ ርምጃ ስለመኖሩ ለቀረበላቸው ጥያቄ አቶ ተወልደ ካለኃይል ተግባር ልጆቹን በሰላም ለመመለስ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

እስካሁን ሁሉንም ታጋቾች ለመመለስ ጊዜ የወሰደበት ምክንያት ምን ሊሆን ይችላል? በሚል በዶይቼ ቬሌ የፌስቡክ ገፅ ላይ ያወያየናቸው አስተያየት ሰጭዎች መንግስት ጉዳዩን ችላ ብሏል የሚለውን ሀሳብ አጉልተዋል። አንዳንዶች መንግስት ሕፃናቱን ለመመለስ የጀመረው ድርድር እና እያደረገው ያለው ጥረት አበረታች ነዉ ሲሉ፣ ሌሎች ደግሞ መንግስት ተጨማሪ የወታደር ሃይል በማስገባት ንፁኃኑን ሕፃናትን መመለስ እንዳለበት ጠቅሰዋል።

መርጋ ዮናስ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic