ከአማረኛ ተናጋሪዉ ጀርመናዊ | ባህል | DW | 02.02.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

ከአማረኛ ተናጋሪዉ ጀርመናዊ

ጀርመናዊዉ አማረኛ ተናጋሪ ዶክተር አንድርያስ ቬተር የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን አጠናቆ ወደ ከፍተና የትምህርት ተቋም ከመግባቱ በፊት የሁለት አመት የሲቪል አገልግሎት ግዴታ ለመወጣት ስራ ላይ ሳለ ነዉ በጎ.አ አስራ ዘጠኝ ዘጠናዎቹ መጀመርያ አፍሪቃን ብሎም ደግሞ ኢትዮጵያን እንደተዋወቃት የገለጸልን።

default

ጀርመናዊዉ አማረኛ ተናጋሪ ዶክተር አንድርያስ

በአለማችን የራሳቸዉ የጽሁፍ ቋንቋ ያላቸዉ አገሮች ከአምስት ወይም ከስድስት እንደማይበልጡ ይታወቃል። በዚህም ምዕራባዉያን ኢትዮጽያ ያራስዋ የጽሁፍ ቋንቋ ሃይማኖት፣ የቀንቀመር ያላት የአስራ ሶስት ወርራትዋ አፍሪቃዊትዋ አገር ሲሉ ይገልጽዋታል።  የሰዉ ዘር መገኛ የሆነችዉን የኢትዮጽያን ታሪክ ለማጥናት ምዕራባዉያን የአማረኛ ቋንቋን የመማር ፍላጎታቸዉ እየጨመረ መምጣቱ ይታያል። በጀርመን በአፍሪቃ ጥናት ምርምር አልያም በሴሜቲክ ተቋም ዉስጥ የአማረኛ ቋንቋ ትምህርት መሰጠቱ አንዱ አካል መሆን ከጀመረም አመታት ተቆጥረዋል። በተለይ በአፍሪቃ ቋንቋ ጥናት ስር እዉቀት ያላቸዉ ምሁራን፣ በጀርመን ዪንቨርስቲ የአማረኛ ቋንቋ በተለይ የግዕዝ ቋንቋ ትምህርት መሰጠት ከጀመረ ከሶስት መቶ አመታት በላይ እንደሆነ ይናገራሉ። እንደዉም የአማረኛ ቋንቋ ትምህርት በጀርመን አገር በዩንቨርስቲ ደረጃ ትምህርት መሰጠት የጀመረዉ የጀርመንኛ ቋንቋ ትምህርት ከመሰጠጡ በፊት እንደሆነ ሲገልጹ በመገረም ነዉ። በአሁኑ ወቅት በጀርመን አገር በበርሊን በሃንቡርግ በላይፕዚግ በማይንዝ በኮለኝ እንዲሁም ሃይደል በርግ ከተሞች ዉስጥ በሚገኙ ዪንቨርስቲዎች የአማረኛ ቋንቋን ይሰጣል በርካታ ምዕራባዉያንም በመማር ላይ ይገኛሉ።

Humboldt-Universität Berlin Dossierbild 2

200ኛ አመቱን ያስቆጠረዉ የበርሊኑ ሁንቦልት ዪንቨርስቲዶክተር አንድርያስ ቬተር በአፍሪቃ ቋንቋዎች ሙዚቃ እና ባህል ዙርያ በርካታ የምርምር ስራዎችን አድርጎአል። ኢትዮጵያዉያንም ከጫፍ እስከ ጫፍ ዞር ጎብኝቶአታል አጥንቷታል። የአዝማሪን ስራ ለጀርመናዉያን ብሎም በአለም አቀፍ መድረክ ለማስተዋወቅ ጥረት ካደረጉት ምሁራን ዉስጥ አንዱ ነዉ። ንጹህ ጀርመናዊ ነዉ። የኢትዮጽያን ባህላዊ ምግቦች እጅግ ቢወድም በተለይ ገንፎ በጣም የሚወደዉ የኢትዮጵያ ባህላዊ ምግብ ነዉ። ከገንፎ ሌላ የበዛወርቅ ትዝታ የዚነት ሙሃባ ዜማ የኤፍሪም ሙዚቃ እጅግ እንደሚያዝናዉ አጫዉቶናል። ኢትዮጽያን ስለሚወድ ቋንቋዋን አጥንቶ ባህልዋን ለምዶ እዚህ በአገሩ በጀርመን በመዲና በርሊን በሚገኘዉ እዉቁ የሁን ቦልት ዪንቨርስቲ በአፍሪቃ በተለይ ደግሞ በኢትዮጽያ የአማረኛ እና በመጥፋት ላይ ባለዉ የአርጎባ ቋንቋ ላይ ጥናት እያደረገ የአማረኛ ቋንቋ በዩንቨርስቲ ዉስጥ ትምህርት ይሰጣል። በጀርመን አገር በተደረገዉ የአዝማሪ ጉባኤ ላይ የአርባ ሶስት አመቱን ጎልማስ ዶክተር አንድርያስ ቬተርን ተዋዉቄዉ ስለነበር እንደዉ ቃለ መጥይቃችንን አንተ እያልኩ ብቀጥል ቅር ይል እንደሁ ንገረኝ አማረኛ የሚናገርን ፈረንጅ አንቱ ማለትም ከበደኝ ስል ነበር ቃለ መጠይቄን የጀመርኩለት ሙሉዉን ቅንብር ያድምጡ!

አዜብ ታደሰ

ተክሌ የኋላ 

Audios and videos on the topic