እስራኤል ስደተኞችን አስገድዳ መመለሷ | ዓለም | DW | 29.10.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

እስራኤል ስደተኞችን አስገድዳ መመለሷ

የእሥራኤል መንግሥት የአፍሪቃን ስደተኞች ለመቀበል ፈቃደኛ እንዳልሆነ በተደጋጋሚ ቢያሳውቅም፤ አሁንም በየቀኑ ስደተኞች የእስራኤልን ድንበር አልፈው ለመግባት ከመሞከር የተቆጠቡበት ጊዜ የለም።

Afrikanische Flüchtlinge in Israel – Viele Flüchtlinge leben in diesem Park im Süden Tel Avivs. DW/Emilie Baujard

Afrikanische Flüchtlinge in Israel

ከሰሞኑ፣  ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ  ስደተኞች፣  መመለስ ግድ እንደሆነባቸው የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ድርጅት ሂውማን ራይትስ ዎች እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች አስታውቀዋል።  እስራኤል ስደተኞች በቀላሉ ወደሀገሯ እንዳይገቡ አጥር ሰርታለች። ይሁንና ስደተኞች ይህንን አጥር አልፈው ለመግባት ይሞክራሉ። ሰሞኑንም ቁጥራቸው በዛ ያለ ስደተኞች በተለይም ኤርትራውያን የእስራኤልን ድንበር ሊሻገሩ ሲሞክሩ ተይዘው ወደ ግብፅ እንዲመለሱ መደረጉ ተዘግቧል።

epa03124957 African refugees pray at a shelter in Tel Aviv, Israel, 27 February 2012. Some 50,000 Africans have entered Israel in recent years, fleeing conflict and poverty in search of safety and opportunity in the relatively prosperous Jewish state. A growing number of African migrants say they were captured, held hostage and tortured by Egyptian smugglers hired to sneak them into Israel. EPA/ABIR SULTAN +++(c) dpa - Bildfunk+++

በእስራኤል የሚገኙ አፍሪቃዊ ስደተኞች በፀሎት ላይ

ስለነዚህ ተመላሽ ስደተኞች እና በእስራኤል ስለሚገኙ ስደተኞች ጊዜያዊ ሁኔታ፦ በዚያችው  ሀገር፣ አፍሪቃውያን ስደተኞችን የሚረዳውና መብታቸውን ለማስከበር የሚንቀሳቀሰው ማዕከል ፤ በምህፃሩ ADRC ዋና ስራ አስኪያጅ፤ አቶ  ዮሐንስ ባዩ ማብራሪያ ሰተውናል።

በጠቅላላው 60000 የሚጠጉ ስደተኞች እስራኤል ውስጥ እንደሚገኙ ይነገራል። እስራኤል ህገ ወጥ የምትላቸውን ስደተኞችን ሰብስባ የምታስቀምጥበት ቦታ እንደምታመቻች ከዚህ ቀደም አስታውቃ ነበር። ይህም እስር ቤት በግንባታ ላይ ነው ይላሉ፤ አቶ ዮሀንስ።

African refugees share breakfast at a shelter in Tel Aviv, Israel Thursday, Feb. 16, 2012. Some 50,000 Africans have entered Israel in recent years, fleeing conflict and poverty in search of safety and opportunity in the relatively prosperous Jewish state. A growing number of African migrants say they were captured, held hostage and tortured by Egyptian smugglers hired to sneak them into Israel.(Foto:Oded Balilty/AP/dapd)

ቴላ ቪቭ የሚገኙ የአፍሪቃ ስደተኞች ቁርሳቸውን ሲመገቡ።

በእስር ቤት ያለው ሁኔታ አስቸጋሪ እንደሆነ በተደጋጋሚ ተሰምቷል። አቶ ዮሀንስ እንደነገሩንም ከሆነ እንደ መስራቤታቸው ያሉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችም ይሁኑ ጠበቆች መግባት አይፈቀድላቸውም። እንደ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር -በምህፃሩ UNHCR ዘገባ 80 ከመቶ የሚሆኑ የኤርትራ ስደተኞች ከለላ በሚጠይቁበት ሀገር እውቅና ያገኛሉ። በእስራኤል ግን ሁኔታው የተለየ ነው።

ምንም እንኳን በቅርቡ በእስራኤል አዲስ ምርጫ የሚካሄድ ቢሆንም መንግስት አላማውን እንደማይቀይር  አቶ ዮሀንስ  እርግጠኛ ናቸው። ስለሆነም በዋና ስራ አስኪያጅነት የሚያገለግሉበት ADRC ለጊዜው ያለው አማራጭ በፍርድ ቤት ለስደተኞቹ ሙግቱን መቀጠል እና ለእናት እና ልጆች መጠለያ ማቅረብ ይሆናል።

ልደት አበበ

ሒሩት መለሰ

Audios and videos on the topic