1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

ኢንጅነር ገበያው እምቢአለ

A-380 የሚባለውን የግዙፉን ኤርባስ አውሮፕላን የተለያዩ ክፍሎች ዲዛይን ካደረጉት መሀንዲሶች አንዱ ናቸው ። በጀርመን የኩባንያው የኢንጅነሪንግ ና የዲዛይን ሥራ በሚከካሄድበት በሰሜን ጀርመኑ የሀምበርግ ከተማ ባለው መሥሪያ ቤት በዚህ ሙያ ከተሰማሩ 15 አመታት አስቆጥረዋል ።ኢንጅነር ገበያው እምቢአለ ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 10:42

ኢንጅነር ገበያው እምቢአለ

የዚህ ግዙፍ አውሮፕላን የተለያዩ አካላት የዲዛይን ስራ በተለየ ትኩረትና ጥንቃቄ እንዲሁም ክትትል ነው የሚከናወነው ።ኤርባስ የስፓኝ የፈረንሳይ የእንግሊዝና የጀርመን የጋራ ኩባንያ ነው ።ኢንጅነር ገበያው እንደሚሉት ከዓለም በግዙፍነቱ የመጀመሪያውን ደረጃ የሚይዘው የዚህ ኩባንያ ምርት የ ኤ-380 አውሮፕላን የተለያዩ አካላት ዲዛይን የሚደረጉትና የሚመረቱትም በነዚህ አራት ሃገራት ውስጥ ነው ።በሚሰሩበት በሃምቡርጉ የኤርባስ የኢንጅነሪንግ ና ዲዛይን መስሪያ ቤት የኢንጅነር ገበያውና የባልደረቦቻቸው የስራ ድርሻ ምን ይሆን ?ኢንጅነር ገበያውተወልደው ያደጉት የአንደኛ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውንም የተከታተሉት ሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ በሚገኘው በቻግኒ ከተማ ነው ። የልጅነት ምኞታቸው ኮሌጅ ወይ ዩኒቨርስቲ መግባት ነበር ። ይህ ምኞታቸው እውን ሆኖ በባህርዳሩ የፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ3 ዓመት አግሮ መካኒክስ ተምረው በከፍተኛ ውጤት በማጠናቀቃቸው እዚያው ኮሌጅ ውስጥ በመምህርነት ማገልገል ጀመሩ ። 2 አመት ካስተማሩ በኋላ ደግሞ የነፃ ትምህርት እድል አግኝተው ጀርመን መጡ ። በበርሊኑ የሁምቦልት ዩኒቨርስቲ መካኒካል ኢንጅነሪንግ ካጠኑ በኋላ በደቡብ ጀርመንዋ ሽቱትጋርት በሚገኝ የኢንጅነሪንግ መሥሪያ ቤት ለሁለት ዓመት ሠርተዋል ።ጀርመን ሲኖሩ ከጀመሩ 27 ተኛ አመታቸውን ያስቆጠሩት ኢንጅነር ገበያው ከተወሰኑ ዓመታት ወዲህ በጀርመን ከአንዳንድ የህብረተሰብ ክፍሎች በኩል የሚንጸባረቀውን የውጭ ዜጎች ጥላቻ የደካሞች አመለካከት ይሉታል ። የውጭ ዜጋም የበኩሉን አስተዋፅኦ በሚያደርግባት በጀርመን ተቀባይነት የሌለው ሲሉም ይቃወሙታል ።ባለትዳርንና የሁለት ልጆች አባት ኢንጅነር ገበያው አሁን ከደረሱበት የሙያ ደረጃ በተጨማሪ ሌላም ምኞት አላቸው ።

ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሰ

Audios and videos on the topic