ኢትዮጵያ እና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አፈፃፀም | ኢትዮጵያ | DW | 23.10.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ እና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አፈፃፀም

መንግሥት «በአገሪቱ የተከሰተውን ብጥብጥ ለማስቆም »አወጣሁት የሚለው አዋጅ ፣በተለይም የአፈፃጸም መመሪያው በአመዛኙ ግልጽነት የሚጎድለው አሻሚ እና የሕዝብ መብትን የሚያፍኑ ከዓለም ዓቀፍ ሕግጋት ጋር የሚፃረሩ አንቀጾች የተካተተበት ነው የሚሉ የሚሉ ትችቶች እየቀረቡበት ነው ። ይህም በዜጎች ላይ ፍርሀት እና ስጋት ማሳደሩ ነው የሚነገረው ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 34:54

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አፈፃፀም

 

ኢትዮጵያ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መተዳደር ከጀመረች ሁለት ሳምንት አለፈ ። በነዚህ ጊዜያትም አዋጁን የማስፈጸም ሥልጣን የተሰጠው ኮማንድ ፖስት ወይም የእዝ ጣቢያ ፣ የአዋጁን አፈፃፀም ዝርዝር መመሪያ አውጥቶ የተለያዩ እርምጃዎችን በመወሰድ ላይ ይገኛል ። ኮማንድ ፖስቱ ፣ በአዋጁ አፈጻጸም መመሪያ መሠረት በተለያዩ ከተሞች «ሁከት» አስነስተዋል ፣በሥራ ማቆም አድማ ተሳትፈዋል የሚላቸውን ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉን፣ አንዳንዶችም እጃቸውን ሰጥተዋል ማለቱን የመንግሥት እና ለመንግሥት ቅርበት ያላቸው መገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል ።እስካሁን የታሰሩትም ቁጥር ወደ 1700 እንደሚደርስ ይነገራል ። የሌሎች ተጠርጣሪዎች ጉዳይም እየተጣራ ነው ተብሏል ። የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዚህ ሳምንት መገባደጃ ያፀደቀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እና አፈፃጸሙ ከየአቅጣጫው ትችቶች እየተሰነዘሩበት ነው ።መንግሥት «በአገሪቱ የተከሰተውን ብጥብጥ ለማስቆም እና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን ለማስከበር »አወጣሁት  የሚለው አዋጅ ፣በተለይም የአፈፃጸም መመሪያው በአመዛኙ ግልጽነት የሚጎድለው አሻሚ እና የሕዝብ መብትን የሚያፍኑ ከዓለም ዓቀፍ ሕግጋት ጋር የሚፃረሩ አንቀጾች የተካተተበት ነው የሚሉ ትችቶች እየቀረቡበት ነው ። ይህም በዜጎች ላይ ፍርሀት እና ስጋት ማሳደሩ ነው የሚነገረው ። በአጭር ጊዜ ውስጥ ጠንካራ ትችቶች የተሰነዘሩበት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እና አፈፃጸሙ የዛሬው እንወያይ ትኩረት ነው ። የድምጽ ማዕቀፉን በመጫን ሙሉ ዝግጅቱን ማድመጥ ይችላሉ።

ኂሩት መለሰ

ልደት አበበ

 

Audios and videos on the topic