ኢትዮጵያዉያን ለምን ይሰደዳሉ?
እሑድ፣ ግንቦት 7 2008ማስታወቂያ
በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉያን ወጣቶች በገፍ ወደ ተለያዩ ሃገራት እየተሰደዱ ነዉ። የተመድ እና ሌሎች የስደተኞች ጉዳይን የሚከታተሉ ዓለም አቀፍ ማኅበራት እንደሚሉት ኢትዮጵያዉያን ወጣቶች ጦርነት እንዳፈረሳት ሶማልያ ወይም ከፍተኛ ጭቆና ይፈጸምባታል ተብላ እንደምትወቀሰዉ ኤርትራ ሁሉ ኢትዮጵያም በርካታ ዜጎችዋ እየተሰደዱ ነዉ። ወደ አዉሮጳ ደቡብ አፍሪቃና ሃረብ ሃገራት ለመግባት የሚሰደዱ ኢትዮጵያዉያን በየአካባቢዉ የሚደርስባቸዉ ግፍና በደል ዘግናኝ መሆኑን በህይወት የተረፉ ስደተኞች ይናገራሉ። ሌሎች ደግሞ በየበረሃዉና በየባህሩ ሞተዉ ይቀራሉ። ለኢትዮጵያዉያን ወጣቶች በገፍ መሰደድ ምክንያቱ ምን እንደሆነ ለማወቅ በየጊዜዉ የሚደረጉ ጥናቶች እና ዉይይቶች ቢኖሩም እስካሁን ድረስ ወጥ ስምምነት ላይ የሚያደርሱ ስምምነቶች የሉም። ወጣቶቹም መሰደዳቸዉን አላቋረጡም። በቅርቡ የሜዲተራንያን ባህር ለማቋረጥ ሲሞክሩ ሰምጠዉ ከሞቱት 500 ያህል ስደተኞች መካከል ከግማሽ የሚበልጡት ኢትዮጵያዉያን ናቸዉ ተብሎ ይታመናል። በዚሁ በያዝነዉ ሳምንት የዛንብያ ፖሊስ 34 ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች ግዛቱን አቋርጠዉ ለማለፍ ሲሞክሩ ይዞ ማሰሩ ይታወቃል። ይህ በቅርቡ የሰማነዉና በምሳሌ የምንጠቅሰዉ ብቻ ነዉ። ኢትዮጵያዉያን ለምን ይሰደዳሉ? የዛሬዉ የምንወያይበት ርዕስ ይሆናል?
አዜብ ታደሰ