የኖርዌ መንግሥት ጥገኝነት የጠየቁ ኢትዮጵያዉያን ስደተኞችን ከሐገሩ ለማባረር ያሰለፈዉን ዉሳኔ በመላዉ አለም የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን እንዲቃወሙ ስደተኞቹ ጠየቁ።
ሽቶልተንበርግ
የኖርዌ መንግሥት ጥገኝነት የጠየቁ ኢትዮጵያዉያን ስደተኞችን ከሐገሩ ለማባረር ያሰለፈዉን ዉሳኔ በመላዉ አለም የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን እንዲቃወሙ ስደተኞቹ ጠየቁ።የኖርዌ መንግሥት ጥገኝነት የጠየቁ ከአንድ ሺሕ የሚበልጡ ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ዉስጥ ወደ ሐገራቸዉ እንዲመለሱ ወስኗል።የስደተኞቹ ተወካዮች እንዳሉት ስደተኞቹ በፈቃዳቸዉ ወደ ሐገራቸዉ ካልተመለሱ መንግሥት አስገድዶ እንደሚልካቸዉ አስጠንቅቋል።ከተወካዮቹ አንዷ ወይዘሪት ዙፋን አማረን በስልክ አነጋግሬያታለሁ።
ነጋሽ መሐመድ
ሸዋዬ ለገሠ