ኢትዮጵያዉን ሥደተኞች ሞትና ስቃይ | ኢትዮጵያ | DW | 01.09.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያዉን ሥደተኞች ሞትና ስቃይ

እስካሁን አስራ-አንዱ ለሞት፥ ቁጥራቸዉ በዉል ያልታወቀ ሌሎችን ለበሽታ እና የተቀሩትን በሙሉ ለስቃይ የዳረገዉ ችግር የሚወገድበት ብልሐት አሁንም ግልፅ አይደለም

default

ጀልባዋ-ሠላም ትገባ ይሆናል ግን እስር ቤትም ሞት አለ

የስዑዲ አረቢያ ፀጥታ አስከባሪዎች ወደ ሐገራቸዉ ለመመለስ ካሰሯቸዉ ኢትዮጵያዉያን መካካል ጂዘን ዉስጥ አምስቱ ከነሱ በፊት ጂዳ ዉስጥ ደግሞ ሌሎች ስድስት መሞታቸዉ በትናንቱ ዜናችንና ከዚያም በፊት ተዘግቧል።ምክንያቱ የእስር ቤቱ ሙቀትና መጨናነቅ ነዉ።የሰዎቹ መሞት ከመሰማቱ በፊት ስደተኞቹ የታሠሩበት ቦታ ለሕይወታቸዉ አደገኛ እንደሆነ በተለያየ ጊዜ ዘግበንም ነበር።ይሁንና እስካሁን አስራ-አንዱ ለሞት፥ ቁጥራቸዉ በዉል ያልታወቀ ሌሎችን ለበሽታ እና የተቀሩትን በሙሉ ለስቃይ የዳረገዉ ችግር የሚወገድበት ብልሐት አሁንም ግልፅ አይደለም።የጂዳዉ ወኪላችን ነብዩ ሲራክ ያነጋገራቸዉ በጂዳ የኢትዮጵያ ቆስልና የኢትዮጵያ ማሕበረሰብ ተጠሪዎች ግን ጉዳዩን እየተከታተልን ነዉ ይላሉ።

ነብዩ ሲራክ

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ

Audios and videos on the topic