የኢትዮጵያ መንግስት የስድስት ታዋቂ ቡና ገዢዎችና አከፋፋዮችን ፈቃድ ከሰረዘ በኋላ አሁን የኢትዮጵያ መንግስት የቡናውን ምርት ራሱ እንደሚሸጥ አስታውቋል።
ስለዚሁ ብዙ ማከራከር ስለያዘው አዲሱ ደምብ ወኪላችን ጌታቸው ተድላ የኮምዩኒኬሽን ሚንስትር አቶ በረከት ስምዖንን እና የኦሮሙያ ቡና ገበሬዎች ህብረት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ታደሰ መስቀላን አነጋግሮዋል። ይሁንና፥ ይኸው መንግስት የቡናውን ምርት ራሱ ለመሸጥ ያወጣው ደምብ የኢትዮጵያ ቡና በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለውን ተቀባይነት እንዳይጎዳ አንዳንድ በዩኤስ አሜሪካና በካናዳ የሚገኙ የቡና አስመጪና አከፋፋይ ኩባንያዎች ስጋታቸውን ገልጸዋል።
ጌታቸው ተድላ/አበበ ፈለቀ/አርያም ተክሌ
ነጋሽ መሐመድ