ኢሬቻ እና አዲሱ ትውልድ | ባህል | DW | 30.09.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

ኢሬቻ እና አዲሱ ትውልድ

በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ እና የተለያዩ ሃይማኖቶችን የሚከተሉ የኦሮሞ ሰዎችን የሚያገናኘው የኢሬቻ በዓል በመጪው እሁድ ይከበራል። በዓሉ በወጣቶች ዘንድ ምን ያክል ይታወቃል? እንዴትስ ይከበራል?

አውዲዮውን ያዳምጡ። 09:33

ኢሬቻ እና አዲሱ ትውልድ

በመጪው እሁድ ከቢሾፍቱ ከተማ አቅራቢያ በሚገኘው ሆራ አርሰዲ ሐይቅ አጠገብ ኢሬቻ ይከበራል። ከአዲስ አበባ ደቡብ ምሥራቅ 45 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ቢሾፍቱ የሚከበረው በዓል ኢሬቻ መልካ ይሰኛል። በዕለተ እሁድ ኦ …. ያ…ማሬዎ….. ማሬዎ እያሉ ፈጣሪን እያመሰገኑ በዓሉን ከሚያከብሩት መካከል የ25ቷ ኩኑ አለማየሁ ትገኝበታለች።

የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ መምህሩ ሰኚ በላቸው ይህን በዓል ሲያከብር የዘንድሮው አራተኛው መሆኑ ነው። ለሰኚ ኢሬቻ ከምዕራባውያኑ የምሥጋና በዓል ጋር ተመሳሳይ ነው። በሰኚ አባባል በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ የኦሮሞ ብሔረሰብ አባላት ኢሬቻን ለማክበር ሲሰበሰቡ ስላለፈው ይወያያሉ። ስለ ነገውም ይመክራሉ።

እሸቴ በቀለ

ሸዋዬ ለገሰ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች