ኢመደበኛው የውጭ ምንዛሪ ገበያ | ኢትዮጵያ | DW | 11.12.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ኢመደበኛው የውጭ ምንዛሪ ገበያ

በኢትዮጵያ «ሬሚተንስ» በያመቱ ከአራት ቢልዮን ዶላር በላይ እንደሚደርስ የዓለም ባንክ ዘገባ ያሳያል። ከዚሁ መካከል ግን ከ95% የሚበልጠው መደበኛ ባልሆነው መንገድ እንደሚላክ በየጊዜው የሚወጡ ዓለም አቀፍ ጥናቶች ውጤት አስታውቀዋል። ስለዚሁ እጅ በእጅ በሚካሄደው ሕጋዊ ባልሆነው የውጭ ምንዛሪ ገበያ ውይይት አካሂደናል። 

«በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገር ቤት የሚልኩት ገንዘብ በ2007 እና በ2008 ዓም  አራት ቢልዮን ዩኤስ ዶላር እንደደረሰ የዓለም ባንክ ዘገባ ያመለክታል። እንደ ዘገባው ግምት፣ «ሬሚተንስ» ከጠቅላላ ብሔራዊው ገቢ መካከል አራት ከመቶውን የሚሸፍን ሲሆን፣ በምጣኔ ሀብቱ ዘርፍ ላይ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል። ገንዘቡ ሀገር ውስጥ በሚገኙ ባንኮች ውስጥ በመተባበር አገልግሎት በሚሰጡ አከፋፋዮች አማካኝነት እንደሚከናወን የብሔራዊ ባንክ መረጃ ያሳያል።  ይሁን እንጂ፣ ብዙዎች ገንዘብ ለመላክ ቀጥተኛ እና  ሕጋዊ ያልሆነውን መንገድ እንደሚመርጡ ነው የሚነገረው። ለምሳሌ፣ በሳውዲ ዐረቢያ በሕጋዊ መንገድ የሚኖሩት ወደ 200,000 የሚጠጉ ኢትዮፕያውያን በየዓመቱ ከ318 ሚሊዮን ዶላር በላይ ወደ ሀገር  እንደሚልኩ ከጥቂት ጊዜ በፊት ባካሄዱት ጥናት አስታውቀዋል። ከዚህ መካከል ብዙው ቁጥጥር በማይደረግበት በአብዛኛው በጥቁር ገበያ ይላካል።

አርያም ተክሌ

ልደት አበበ

Audios and videos on the topic