አዉሮጳዉያን ባሪያ ፈንጋዮችና የካሳ ጥያቄ | ዓለም | DW | 31.07.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

አዉሮጳዉያን ባሪያ ፈንጋዮችና የካሳ ጥያቄ

ማሕበሩ በተለይ ብሪታንያ፥ ፈረንሳይና ዳች (ወይም ኔዘርላንድን) ካሳ እንዲከፍሉ በሕግ ሊሞግታቸዉ ተዘጋጅቷል።ጠበቆች፥ አንዳድ ሙሑራንና የመብት ተሟጋቾችም የማሕበሩን አቋም እንደሚጋሩ እየተናገሩ ነዉ

 አዉሮጳዉያን ቅኝ ገዢዎችና ተስፋፋዊች አፍሪቃዉያንን እየፈነገሉ በባሪያነት በመሸጥ በመለወጣቸዉ ለዋሉት ግፍ ካሳ እንዲከፍሉ አስራ-አራት የካረቢክ አካባቢ ሐገራት የመሠረቱት ማሕበር ጠየቀ።ማሕበሩ እንደሚለዉ የአዉሮጳ ቅኝ ገዢዎችና ባሪያ ፈንጋዮች በጥንታዊ አፍሪቃዉያን ላይ የፈፀሙት ኢሠብአዊ ግፍ አሁን በካረቢክም ሆነ በተቀረዉ ዓለም ለሚገኘዉ ጥቁር ሕዝብ መደኽየትና ኋላ ቀርነት ዋና ምክንያት ነዉ።ማሕበሩ በተለይ ብሪታንያ፥ ፈረንሳይና ዳች (ወይም ኔዘርላንድን) ካሳ እንዲከፍሉ በሕግ ሊሞግታቸዉ ተዘጋጅቷል።ጠበቆች፥ አንዳድ ሙሑራንና የመብት ተሟጋቾችም የማሕበሩን አቋም እንደሚጋሩ እየተናገሩ ነዉ።የለንደንዋ ወኪላችን ሐና ደምሴ አጭር ዘገባ ልካልናለች።

ሐና ደምሴ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic