የደቡብ አፍሪቃ ገዢ ፓርቲ የአፍሪቃ ብሔራዊ ምክር ቤት በእንግሊዘኛው ምህፃር «ANC» ሰሞኑን ባደረገዉ ግምገማ በተለያዩ ችግሮች የተተበተቡት ፕሬዚዳንት ጄኮብ ዙማ ከሥልጣናቸዉ ይዉረዱ የሚለዉን ሀሳብ አለመቀበሉን ገለፀ ።
ዴሞክራቲክ አልያንስ ወይም « ዴሞክራሲያዊ ህብረት » በእንግሊዘኛው ምህጻር «DA» የተባለው የደቡብ አፍሪቃ መንግሥት ዋነኛ ተቃዋሚ ፓርቲ በበኩሉ ፕሪዚዳንት ዙማን ለማዳን ሲባል ሃገሪቱ እየተጎዳች ነዉ ሲል አቤቱታዉን አሰምቷል። ምሑራን፤ የተለያዩ የሲቪክ ማኅበራት፤ የሃይማኖት አባቶች፤ የፓርቲዉ መሥራቾችና ለበርካታ ዓመታት በነጻነት ትግል የተሳተፉ በተለያዩ የስራ መስኮች በኃላፊነት የሠሩና የተሰናበቱ 106 ነባር ታጋዮች ተሰባስበዉ በሃገሪቱ ያሉ ችግሮች መንስዔ ናቸዉ ላሏቸዉ ለፕሬዚዳንት ጄኮብ ዙማ አቤቱታቸዉን በማቅረብ ከሥልጣን እንዲወርዱ ግፊት ሲያደርጉ ቆይተዋል። ዝርዝሩን የጆሀንስበርጉ ዘጋቢያችን መላኩ አየለ ልኮልናል።
መላኩ አየለ
አዜብ ታደሰ
ኂሩት መለሰ