አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትኅ ፓርቲ የሰጠው መግለጫ፣ | ኢትዮጵያ | DW | 27.02.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትኅ ፓርቲ የሰጠው መግለጫ፣

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትኅ ፓርቲ፣ «መንግሥት፣ ያወጣውን ሀገ-መንግሥት የማክበርና የማስከበር ኀላፊነት አለበት፣ ይህንን ኀላፊነቱን ግን በሚገባ እየተወጣ አይደለም።

default

ከኢትዮጵያ መልክዓ-ምድራዊ ገጾች አንዱ፣

በዚህም ምክንያት፣ የዜጎች መሠረታዊ መብቶች እየተጣሱ ነው፣ ሲል በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ አስታወቀ።

ፓርቲው፣ ይህን ያስታወቀው፣ «መንግሥት፣ ህገ-መንግሥታዊ ድንጋጌዎችን እያከበረና እያስከበረ አይደለም » በሚል ርእስ ባወጣው መግለጫ ላይ ሲሆን፣ ፓርቲው፣ የመደራጀትና በነጻነት የመንቀሳቀስ ህገ-መንግሥታዊ መብቱ እየተጣሰ መሆኑን፣ የፓርቲው መሪ፣ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ፣ ዳግም የታሠሩበት ድርጊትም፣ በህግ ጥሰት የታጀበ መሆኑን፣ አንድነት ፣ ለዴሞክራሲና ለፍትኅ ፓርቲ ገልጿል።

ታደሰ እንግዳው ዝርዝር ዘገባ አለው።

Tekle Yewhala/Hirut Melesse