አምነስቲ ወጣቶች በብዛት የታሰሩበትን ሁኔታ አወገዘ
ማክሰኞ፣ መስከረም 15 2011ማስታወቂያ
መንግሥት ስርዓት ለማስከበር ርምጃ መውሰዱ ትክክል ቢሆንም ሕግን ባከበረ መንገድ መሆን እንዳለበት የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምሥራቅ አፍሪቃ የሰብአዊ መብት አጥኚ አቶ ፍሰሐ ተክሌ ዛሬ ለዶይቸ ቬለ ተናግረዋል። ወደ ጦር ማሰልጠኛ ቦታዉ ወደ ጦላይ የተወሰዱት ወጣቶች የሰብዓዊ መብታቸዉ እና የመንቀሳቀስ መብታቸዉ መጣሱን፣ እንዲሁም፣ ጫትና ሺሻ በሃገሪቱ ደንብ ሕገ ወጥ ነዉ በሚል የወጣ ምንም ዓይነት ሕግ አለመጽደቁንም አቶ ፍስሐ አክለው አስታውቀዋል።
አርያም ተክሌ
ሸዋዬ ለገሠ