አሜሪካ የአርባ ምንጭ ሰው አልባ አውሮፕላን ተልዕኮን ዘጋች | ኢትዮጵያ | DW | 03.01.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

አሜሪካ የአርባ ምንጭ ሰው አልባ አውሮፕላን ተልዕኮን ዘጋች

ዩናይትድ ስቴትስ አርባ ምንጭ፤ ኢትዮጵያ ይገኝ የነበረው የሰው አልባ አውሮፕላን ተልዕኮዋን መዝጋቷን አንድ የኤምባሲ ባለሥልጣን አስታወቁ። የዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ ሠራተኞች ከእንግዲህ አርባ ምንጭ እንደማይኖሩ ዩናይትድ ስቴትስ አስታውቃለች።

ኢትዮጵያ የሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ቃል-አቀባይ ዴቪድ ኬኔዲ የአርባ ምንጩ ሰው አልባ አውሮፕላን ማዕከል ከአሁን በኋላ አስፈላጊ አይደለም ሲሉ በኢሜል መልእክት መግለፃቸቸውን አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል። «የዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ ሠራተኞች ከእንግዲህ በአርባ ምንጭ የሉም» ሲሉም ቃል አቀባዩ አክለዋል። ዩናይትድ ስቴትስ የሶማሊያው ጽንፈኛ ታጣቂ ቡድን አልሸባብ ላይ ቅኝት እና ጥቃት ለመሰንዘር ትጠቀምበታለች የተባለው የአርባ ምንጭ ማዕከል ስለመኖሩ በይፋ አረጋግጣ አታውቅም። ኢትዮጵያ የአልሸባብ ታጣቂ ቡድንን ለመዋጋት ወታደሮቿን ወደ ሶማሊያ ማዝመቷ አይዘነጋም። ምንም እንኳን የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ኢትዮጵያን በሰብአዊ መብቶች ጥሰት በተደጋጋሚ ሲወቅሱ ቢሰማም፤ ኢትዮጵያ ዩናይትድ ስቴትስ በምሥራቅ አፍሪቃ በምታካሂደው ፀረ-ሽብር ዘመቻ ዋነኛ ተባባሪ ናት።

እሸቴ በቀለ

ማንተጋፍቶት ስለሺ