አለም- አዲሱ የጎርጎረሳዉያኑ 2012 አመት አቀባበል | ዓለም | DW | 01.01.2012
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

ዓለም

አለም- አዲሱ የጎርጎረሳዉያኑ 2012 አመት አቀባበል

በአለም ዙርያ ያሉ ነዋሪዎች አዲሱን የጎርጎረሳዉያን 2012 አ.ም በደማቅ የሙዚቃ ድግስ እና ህብረቀለም በሚተፉ ርችት ተኩስ ተቀበሉ።

በአለም ዙርያ ያሉ ነዋሪዎች አዲሱን የጎርጎረሳዉያን 2012 አ.ም በደማቅ የሙዚቃ ድግስ እና ህብረቀለም በሚተፉ ርችት ተኩስ ተቀበሉ። በቀን ለሊት ለዉጥ መቀያየር ምክንያት በመጨረሻ አዲሱን አመት የተቀበሉት ዩናይትድ ስቴትስ ዉስጥ ያሉ ነዋሪዎች መሆናቸዉ ተመልክቶአል። በኒዉ ዮርኩ ታይምስ ስኩየር ላይ በመቶ ሽዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች አዲሱን አመት በደማቅ መቀበላቸዉ ተነግሮአል። የጀርመንዋ መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል ለህዝባቸዉ ባሰሙት የእንኳን አደረሳችሁ መልክት በአዉሮጳ በዩሮ ተጠቃሚ አገሮች የየዕዳ ቀውስ ቢከሰትም ህብረተሰቡ በህብረት መቆም እንደሚገባዉ አስታዉቀዋል። መራሂተ መንግስቷ ከዕዳ ቀዉሱ ለመዉጣት ገና ረጅም እና ከባድ ጉዞን እደሚጠይቅ አስታዉሰዉ አዉሮጳ ከችግሩ በጥንካሪ እንደሚወጣ ያላቸዉን እምነት ገልጸዋል። በሌላ በኩል ሜርክል በጀርመን ከቅርብ ሳምንታቶች ወዲህ ይፋ የወጣዉ አንድ የቀኝ አክራሪዎች ቡድን ያደረገዉን የግድያ ወንጀል በማሰብም ህዝባቸዉ በጥሞና እና በመተሳሰብ በጋራ እንዲቆም ጠይቀዋል
(የሟች ቤተሰብ የደረሰባቸዉን ሃዘን ፍቀን እንደነበረ ማድረግ እንደማንችል እናዉቃለን። ግን እናንተ እና እኛ ባጠቃላይ ሁላችንም ወንጀሉን በግልጽ እና በዝርዝር ለመመርመር እና ወንጀለኞችን እና የወንጀሉን ተባባሪዎች ህግ ፊት የማቅረብ ሃላፊነት አለብን)
በጀርመን ዋንኛዉ የአዲስ አመት ፊስታ የተካሄደዉ በርሊን በሚገኘዉ ብራንድ ቡርገር ቱር በተሰኝዉ ሰፊና ረጅም አደባባይ ላይ ሲሆን አዲስ አመትን ለመቀበል እና ሪችት ለመተኮስ ከአንድ ሚሊዮን ህዝብ በላይ መገኘቱ ተገልጾአል።

አዜብ ታደሰ
ማንተጋፍቶት ስለሺ

 • ቀን 01.01.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink http://p.dw.com/p/13cba
 • ቀን 01.01.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink http://p.dw.com/p/13cba