ቴክኖሎጂና ወጣት አካል ጉዳተኞች | ባህል | DW | 05.04.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

ቴክኖሎጂና ወጣት አካል ጉዳተኞች

አዲስ ቴክኖሎጂ በአካል ጉዳተኞች ህይወት ውስጥ ምን አይነት ሚና ይጫወታል? በኢትዮጵያስ ምን ያህል ተስፋፍቷል ማለት ይቻላል?

Das Forschungsprojekt HyperBraille entwickelt mit dem zweidimensionalen Braille-Flächendisplay eine Art grafikfähigen Laptop für Blinde und Sehbehinderte sowie die zu dessen Ansteuerung notwendige Software, Filter für Anwendungsprogramme und Browser. Zeitgleiche Anwendertests und neue Schulungskonzepte sollen sehbehinderte Computernutzer an die neuen Möglichkeiten des Umgangs mit dem Computer heranführen. HyperBraille wird vom Bundesministerium für Wirtschaft und Technologie gefördert (BMWi). Das Fördervolumen beträgt 4,1 Millionen Euro.

በተለይ በምዕራቡ አለም አካል ጉዳተኞች ቴክኖሎጂን ተጠቅመው ህይወታቸውን ልክ እንደ ማንኛውም ሰው ሲመሩ ይስተዋላል። ጋዜጠኛ ቴድሮስ አይነ ስውርም ስለሆነ ጉዳዩን በቅርበት ይከታተላል።

ቴድሮስ ለአይነ ስውራን የሚሆኑ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ሲወጡ እየተከታተለ አጠቃቀማቸውንም ይሞክራል። ሀገሪቷ ባላት የቴክኖሎጂ አቅርቦት ልክ፣ የገንዘብ እና የአስተሳሰብ አቅም አካል ጉዳተኞች የቴክኖሎጂው ተጠቃሚ እንደሆኑ ቴድሮስ ይናገራል። ይሁንና ኢትዮጵያ ውስጥ በአጠቃላይ ለአካል ጉዳተኞች ጠቃሚ የሚባለው ቴክኖሎጂ ምንም ያህል እንዳልተስፋፋ ነው የሚናገረው።

አይነ ስውራን ኢንተርኔት በመጠቀም አዲስ ስለሚወጡ ቴክኖሎጂዎች፣ እና ስልቶች ከሌሎች በአለም ዙሪያ ካሉ ፤ማየት ከማይችሉ እና ከሚችሉ ሰዎች ጋ ሀሳብ መለዋወጥ ይችላሉ። ለምሳሌ ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ አይነ ስውራን እየተማሩት ስላለው

የክሊክሶናር የድምፅ አወጣጥ ስልት። የሚያስተጋባውን የገዛ ድምፃቸውን መልሰው በማስተዋል ከግንብ ፣ዛፍ እና ሌሎች ነገሮች ፊት ቆመው እንደው መለየት ይችላሉ።

ቴክኖሎጂ አይነ ስውራንንም ይሁን ሌሎች አካል ጉዳተኞች ጥገኛ ሳይሆኑ እንዲንቀሳቀሱ መንገድ ቢፈጥርም፤ በአግባቡ ያለማስተዋሉ ሁኔታ፤ እንኳን ጉዳተኞችን ማንኛውንም ሰው አደጋ ውስጥ የሚጥሉ ናቸው። ወደፊት በአካል ጉዳተኞች ላይ በማወቅ ወይንም ባለማወቅ የሚፈፀሙት የመብት ጥሰቶች እንዲቆሙ ምን መደረግ አለበት? ለመብት ጥሰቱ መንስኤ የአመለካከት ችግር እንደሆነ ቴድሮስ ያስረዳል።

ቴክኖሎጂ ለወጣት አካል ጉዳተኞች ስለሚጫወተው ሚና ከጋዜጠኛ ቴድሮስ ፀጋዬ ጋ በወጣቶች አለም ያደረግነውን ቆይታ ከዚህ በታች ማድመጥ ይቻላል።

ልደት አበበ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic