ታዳሽ የኃይል ምንጭ | ጤና እና አካባቢ | DW | 27.06.2008
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ጤና እና አካባቢ

ታዳሽ የኃይል ምንጭ

ኢትዮጵያ ከተክል ለሚገኘዉ ታዳሽ ኃይል ማልትም ባዮ ፊዩል ትኩረት ሰጥታለች፤ በየዓመቱም ከሸንኮራ ብቻ አንድ ቢሊዮን ሊትር ኤታኖል ለማምረት ታልሟል።

default

ለተፈጥሮ ነዳጁ የሚዉል ተክል

ለታዳሽ የኃይል ምንጭነት ከሸነኮራ አገዳ በተጨማሪ የማሽላና የበቆሎ አገዳዎች፤ እንዲሁም የጉሎ ዛፍ፤ ጃትሮፋ የተባለዉ ተክልና የዘንባባ ዛፍም ይዉላሉ። ከእነሱ የሚገኘዉም ፍሳሽ መሆኑን ባለሙያዉ አቶ መልስ ተካ አስረድተዋል። ኢትዮጵያ በዋናነት ይህን የታዳሽ ኃይል ለመጠቀም ያለመችዉ አንድም ለነዳጅ የሚወጣዉን የዉጭ ምንዛሪ ለመቆጠብ፤ አማራጭ የኃይል ምንጭ ለማጠናከርና ብክለትንም ለመከላከል ነዉ።