ታቅዶ የከሸፈዉ የስልጣን ሽግግር በየመን | ዓለም | DW | 19.05.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

ታቅዶ የከሸፈዉ የስልጣን ሽግግር በየመን

ትናንት በየመኑ ፕሬዝደንት እና በተቃዋሚዎቻቸዉ መካከል ይፈረማል ተብሎ የተጠበቀዉ የስልጣን ሽግግር ስምምነት ከሽፏል።

default

የባህረ ሰላጤዉ ሀገራት ምክር ቤት

ስምምነቱ ምንም እንኳን ፕሬዝደንት አሊ አብደላ ሳልህን ያለመከሰስ መብት አስከብሮ በክብር ከስልጣን መንበር የሚነሱበትን መንገድ ያመቻቻል ተብሎ ቢታሰብም ዘገባዎች እንዳመለከቱት ሳልህ ፈቃደኛ ባለመሆናቸዉ ሳይፈረም ቀርቷል። ስምምነቱን ያመቻቹት የባህረ ሰላጤዉ ሀገራት ምክር ቤት ሚኒስትሮች በመጪዉ ቀናት ዳግም ሪያድ ላይ እንደሚሰበሰቡ ሲገለፅ የመናዉያን ተደራዳሪዎቹ ይገኙ እንደሁ ግን የተገኘ መረጃ የለም። ይህ በእንዲህ እንዳለም የአሜሪካን ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ በየመን የስልጣን ሽግግር እንዲደረግ አሳስበዋል። ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት የፊታችን እሁድ በየመን ተቀናቃኝ ወገኖች መካከል ለሁለተኛ ጊዜ ተሞክሮ የከሸፈዉ ስምምነት ሊፈረም ይችላል።

ነብዩ ሲራክ

ሸዋዬ ለገሠ

ሂሩት መለሠ