1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ተቃዋሚ ፓርቲዎች፤ የውስጥ ችግሮቻቸውና ተፅእኖው

ተቃዋሚዎች የሚከፋፍል የሚያጋጫቸው በአንድ ላይ ፀንተው እንዳይቆሙም የሚያደርጋቸው ገዥው ፓርቲ ኢህአዲግ መሆኑን በተለያዩ አጋጣሚዎች ይገልጻሉ። ተቃዋሚዎችን እንደማይጫን የሚናገረው መንግሥት በበኩሉ ችግራቸው የተሻሉ አማራጭ የፖለቲካ መርሃ ግብሮችን ይዘው መቅረብ አለመቻላቸው ነው ሲል የትግል ስልታቸውን ያጣጥላል ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 27:49

ተቃዋሚ ፓርቲዎችና የውስጥ ችግሮቻቸው

የኢትዮጵያ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሃገሪቱ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ የሚጠበቅባቸውን ድርሻ ባለመወጣት ተደጋጋሚ ትችቶች ይቀርቡባቸዋል ። ከተቃዋሚ ፓርቲዎች አባዛኛዎቹ ከመጠናከር ይልቅ እየተዳከሙ መሄዳቸው ተግባብተው ከመሥራት ይልቅ በትልቁም በትንሹም መናቆር መለያያቸው ሃላፊነታቸውን እንዳይወጡ ከፖለቲካው መድረክ እንዲገፉም አድርጓል ሲሉ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ወገኖች ይተቻሉ ። ተቃዋሚዎች በበኩላቸው የአብዛኛዎቹ ችግሮቻቸው መንስኤ ከመንግሥት በኩል ይደርሱብናል የሚሏቸው ተጽእኖዎች መሆናቸውን ይናገራሉ ። የሚከፋፍል የሚያጋጫቸው በአንድ ላይ ፀንተው እንዳይቆሙም የሚያደርጋቸው ገዥው ፓርቲ ኢህአዲግ መሆኑን በተለያዩ አጋጣሚዎች ይገልጻሉ። ተቃዋሚዎችን እንደማይጫን የሚናገረው መንግሥት በበኩሉ ችግራቸው የተሻሉ አማራጭ የፖለቲካ መርሃ ግብሮችን ይዘው መቅረብ አለመቻላቸው ነው ሲል የትግል ስልታቸውን ያጣጥላል ።የዛሬው እንወያይ በተቃዋሚ ፓርቲዎች የውስጥ ችግሮችና ተፅእኖአው ላይ ያተኩራል ።

ኂሩት መለሰ

ልደት አበበ

Audios and videos on the topic