ብቸኛዋ አይሮፕላን አብራሪ ምሩቅ | ባህል | DW | 21.06.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

ብቸኛዋ አይሮፕላን አብራሪ ምሩቅ

የኢትዮጲያ አየር መንገድ ተቀጥራ ለመስራት በዝግጅት ላይ ናት። ወጣት ሰላም ተስፋዬ። «የኢትዮጵያ ኤርላይንስ አቪዬሽን አካዳሚ »በቅርቡ አሰልጥኖ በአይሮፕላን አብራሪነት ካስመረቃቸው አንዷ ናት።

default

አይሮፕላን አብራሪዋ ሰላም ተስፋዬ

ሰላም ተስፋዬ የ24 አመት ወጣት አይሮፕላን አብራሪ ናት። አዲስ አበባ ነው ተወልዳ ያደገችው። ትምህርቷን እዛው አዲስ አበባ መሚገኙ ት/ቤቶች ከተከታተለች በኋላ፤ ለከፍተኛ ትምህርት ወደ አርባ ምንጭም አምርታ ነበር። እዛም በኤሌክትሪካል ኢንጂነሪግ ተመርቃለች። ከምህንድስና ወደ አይሮፕላን አብራሪነት፤ እንዴት? መልስ ሰጥታናለች።

ሰላም የአይሮፕላን አብራሪነትን ስልጠና ለመውሰድ ወሳኝ የነበረውን 1 ሜትር ከ70 ቁመት እስከምታሟላ በባንክ ውስጥ ለ 9 ወር ያህል ታገለግል ነበር። የአይሮፕላን አብራሪነት ትልቅ ኃላፊነትን የሚጠይቅ ሙያ መሆኑን አውቃ ነው ወደ ስልጠናው የገባችው።

ይህ የስልጠና ፕሮግራም ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ብቻ ሳይሆን ከአፍሪቃ የበረራ ማሰልጠኛዎችም የመጀመሪያው እንደሆነ ይነገርለታል። ፕሮግራሙ« ፍላይት ፓዝ ከሚባል የካናዳ መስሪያ ቤት ጋ በትብብር እንደቀረበ እና እነ ሰላም አሜሪካዊ እና ኢትዮጵዊ አይሮፕላን አብራሪዎች እንዳሰለጠኗቸው ሰላም ገልፃልናለች።

ሰላም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን የተከታተለችው ሴቶች ብቻ በሚማሩበት ትምህርት ቤት ነው። አሁን ደግሞ የ 19 ወር ቆይታዋ ከ25 ወንዶች ጋ ነበር። በአይሮፕላን አብራሪነት ስልጠናው ብቸኛ ሴት በመሆኗ የተለየ ነገር ገጥሟት ይሆን? ወጣቷ 19 ወር በቆየው ስልጠናዋ ስለነበራት ጊዜ፣ ስራ እና ተሞክሮ ለመስማት የድምፅ ዘገባውን ይጫኑ።

ልደት አበበ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic