ብርቁ፣ የቬኑስና የፀሐይ ትርዒት፣ | ሳይንስ እና ኅብረተሰብ | DW | 07.06.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ሳይንስ እና ኅብረተሰብ

ብርቁ፣ የቬኑስና የፀሐይ ትርዒት፣

ጭጋግ ፣ ደመና ፣ ዝናም በሌለበት ፍንትው ባለ ሰማይ ፤ ቀን ፀሐይን፣ ሌሊት ጨረቃንና ከዋክብትን ፣ የተወርዋሪ ከዋክብትን መወንጨፍና የመሳሰለውን የተፈጥሮ ትርዒት በአድናቆት ለመከታተል አመቺነቱ አያጠራጥርም። አልፎ -አልፎ ደግሞ የፀሐይ ግርጃን

ከትናንት እስከ ዛሬ ማለዳ ፤ ለምድራችን የቅርብ ጎረቤት የሆነችው ፕላኔት ፣ ቬኑስ (አጥቢያ ኮከብ)፣
በፀሐይ አካል ላይ የምንትሸራተት በመምሰል ጥቁር ነጥብ መስላ
ስትሸጋገር በዓለም ዙሪያ ታይታለች ከዚሁ ልዩ የተፈጥሮ ትርዒት ጋር በማያያዝ ስለ
ቬኑስ ሳይንስና ኅብረተሰብ የሚያቀርበው ዝግጅት አለው ።

ጭጋግ ፣ ደመና ፣ ዝናም በሌለበት ፍንትው ባለ ሰማይ ፤ ቀን ፀሐይን፣ ሌሊት ጨረቃንና ከዋክብትን ፣ የተወርዋሪ ከዋክብትን መወንጨፍና የመሳሰለውን የተፈጥሮ ትርዒት በአድናቆት ለመከታተል አመቺነቱ አያጠራጥርም። አልፎ -አልፎ ደግሞ የፀሐይ ግርጃን የመሳሰለ ተጨማሪ ትርዒት የመመልከት ዕድልም ያጋጥማል። ከትናንት እስከዛሬ ፤ ጎህ እስኪቀድ ድረስ፤ ከምዕራብ እስከ ምሥራቅ ፤ ከአሜሪካ እስከ እስያና ፖሊኔሺያ፤ 6 ሰዓት ከ 40 ደቂቃ የወሰደ አንድ ልዩ የተፈጥሮ ትርዒት ተከሥቶ ነበር።

በሰሜን አሜሪካ ፣ ቀን፤ ሌሊቱን፣ ለዛሬ አጥቢያ ደግሞ፣ በማዕከላዊው አውሮፓ፣ ከ 10 ሰዓት ከ45 ደቂቃ (4: 45)አንስቶ እስኪነጋ 1 ሰዓት (7 00) ገደማ ድረስ ፣ በዚህ በያዝነው ምዕተ ዓመት ለመጨረሻ ጊዜ፣ ማታና ጎህ ሲቀድ ለምድራችን ቀረብ ብላና ደምቃ የምትታየው አጥቢያ ኮከብ (ቬኑስ)፣ ነጭ ዝርግ ሳህን በመሰለችው ፀሐይ፣ ከሩቅ ለሚያያት ጥቁር ነቁጥ መስላ ፣ ምኅዋሯን እንደጠበቀች፣ ፀሐይን አልፋ ስትጓዝ ታይታለች። መጠናቸው ሲነጻጸር ፤ ቬኑስ የፀሐይን 1/30ኛ መሆንዋ ነው። ቬኑስ በተሟላ ግርጃ ፀሐይን ልትሸፍን አልቻለችም። በጀርመን ሀገር፣ ከበርሊን ፤ ሃምበርግ፤ ኮሎኝና ሙዩኒክ ድረስ ፤ የተወሰኑ ጉጉዎች ብቻ ናቸው በሌሊት ተነስተው የተባለውን ትርዒት የተመለከቱ! ይህ ለሥነ ፈለክ ተመራማሪዎች የተፈጥሮ ትርዒት ሆኖ የታየው ከፀሐይ ትይዩ፣ የቬኑስ ቀስ ብሎ መሸጋገር (Venus Transit)ከእንግዲህ የሚታየው ከ 105 ዓመት በኋላ ፤ እ ጎ አ ታኅሳስ 11 ቀን 2117 ዓ ም ነው።

የሩቁን አቅርቦ የሚያሳየው ልዮ መነጽር ቴሌስኮፕ በመካከለኛው ዘመን ከተሠራ ወዲህ፤ ከፕላኔቶች ሁሉ ለምድራችን የምትቀርበው፣ በመጠንም የምትመሳሰለውን ፕላኔት፣ እኛ አጥቢያ ከከብ የምንላትን ቬኑስ ፣ በውስጣዊው ምኅዋር ለምድራችንና ለፀሐይ ቀረብ ብላ፣ ፀሐይን በትይዩ አቋርጣ ስትሻገር ፣ እ ጎ አ ከ 1639 እስከ 2012 ፤ ባለፉት 371 ዓመታት ገደማ እስከዛሬ ደረስ ማለት ነው መመልከት የተቻለው 7 ጊዜ ብቻ ነው።

በ 1639, 1761, 1769, 1874 ,1882, 2004 እና 2012!

ይኸው አጥቢያ ኮከብ ፀሀይን የምታቆራርጥበት ጉዞ፣ የ 18ኛውና 19ኛው ክፍለ ዘመን የሥነ ፈለክ ጠበብት ፤ ምድራችን ከፀሐይ ያላትን ርቀት ለመለካት እንደበጃቸው ይነገራል።

በጥንት ሮማውያን አማልእክት፣ የፍቅር ጣዖት ሆና ትታሰብ የነበረችው፤ ቬኑስ ስሟን ያገኘችው ከዚሁ አምልኮ ጋር በተያያዘ ነው። ማታና ጎህ ሲቀድ ጎልታ የምትታየው ቬኑስ፣

ጥንት ከምድር ጋር እንደ መንትያ ፕላኔት ትታይ እንደነበረ ቢታወቅም፤ የኅዋ ምርምር ጉዞ ከተጀመረ ወዲህ ፣ መቶ በመቶም ባይሆን ስለ ቬኑስ ብዙ ማወቅ ተችሏል። እ ጎ አ ከ 1970 በፊት ለ 10 ዓመታት ያህል የቀድሞዋ ሶቭየት ኅብረትና ዩናይትድ እስቴትስ መረጃ ሰብሳቢ መንኮራኩሮችን በተደጋጋሚ ወደ ቬኑስ ማምጠቃቸው አልቀረም። ይሁንና በተጠቀሰው ዓመት በተሳካ ሁኔታ ቬኑስ ላይ ለማረፍ የበቃችው VENERA 7 የተሰኘችው የሶቭየት አሳሽ መንኮራኩር ያስተላለፈችው መረጃ ፣ ያኔ ፣ የምድር እኅት እየተባለች ትሞካሽ የነበረችው ቬኑስ ተስፈኞች የሥነ ፈለክ ጠበብትን ሁሉ ኩምሽሽ ነበረያደረገቻቸው።

ቬኑስ ወቅያኖሶቿ ተነው ያለቁባት ነጎድጓድና መብረቅ ዘወትር የሚከሠትባት፤ድኝና የድኝ አሲድ እጅግ በበዛበት ከባድ ቢጫማ ደመና የተሸፈነች፤ እጅግ ኃይለኛ ወጀብ የማይለያት ፣ ለፀሐይ ከሁሉም ከምትቀርበው ከሜርኩሪ የባሰ የሙቀት መጠን ያላት ፣ በዚህም ሳቢያ ሲዖል ልትሰኝ የምትችል ናት። እንበል ፣ ይሞከር ተብሎ አንድ ጠፈርተኛ ፣ እንኳን መሬቷን ቢረግጥ፤ እጅግ ኃይለኛ በሆነው ግለቷ ፤ ተኮማትሮ ፣ ከመቅጽበት እንደ ስብ ቀልጦ ነው ህይወቱን የሚያጣው። የቬኑስ ግለት የእርሳስ ማዕድንንም ከመቅጽበት የሚያቀልጥ መሆኑ ነው የሚነገርለት።

ተክሌ የኋላ

ሸዋዬ ለገሰ

Audios and videos on the topic