1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

ቡርኪና ፋሶ የፊልም ፊስቲቫል

በምዕራብ አፍሪቃይቷ ቡርኪና ፋሶ የተካሄደዉ FESPACO የፊልም ፊስቲቫል ከሁለት መቶ በላይ አፍሪቃዉያን የፊልም ባለሞያዎች ተገኝተዋል

በዋጋዱጉ የፊልም አዳራሽ

በዋጋዱጉ የፊልም አዳራሽ

ቡርኪና ፋሶ ዋና ከተማ በዋጋዱጉ ለሃያኛ ግዜ የተዘጋጀዉ FESPACO የፊልም ፊስቲቫል በመዲናቷ ታላቅ የመነጋገርያ ርዕስ ሆኖ ነበር የከረመዉ። የከተማዋን ወበቃማ የአየር ጸባይ፣ አቧራማዉን ንፋስ ወደጎን ትቶ ፊስቲቫሉን ሊካፈል የመጣ ጋዜጠኛ የፊልም ባለሞያ እንዲሁም ሌሎች ታዳምያን እርስ በርሱ ከየት አገር ነዉ የመጣኸዉ እንዴት አገኘኸዉ ዝግጅቱን የትኛዉ ፊልም ነበር የማረከህ በመባባል አድናቆታቸዉን ሲገላለጹ ታይቶአል። እንደ በርሊኑ ወይም እንደ ሎሳንጀለሱ የፊልም ፊስቲቫል በቀይ ምንጣፍ የፊልም ተዋናይ ደምቀዉ እና አሸብርቀዉ ባይታዩም በዋጋዱጉ በተዘጋጀዉ የፊልም ፊስቲቫል በአዳራሽ ፊልሞች ታይተዋል። ፋሮ ማለት የዉሃ ንጉስ የተሰኘዉ ፊልም አንድ ከአገሩ ወጥቶ የሚኖር የማሊ ተወላጅ ያለ ምንም ጥሩ ዉጤት በፊት ወደ ሚኖርበት የገጠር ከተማ ሲመለስ የሚተርከዉ ፊልም ሌላዉ አንዳንድ ልምዳዊ የሆኑ አምልኮቶች ተቀባይነታቸዉን እያጡ መምጣታቸዉን የሚያመላክቱ ፊልሞች ታይተዋል።