በጋምቤላ የታገቱት ህፃናትና ሴቶች | ኢትዮጵያ | DW | 29.04.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

በጋምቤላ የታገቱት ህፃናትና ሴቶች

የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ከደቡብ ሱዳን ወደ ጋምቤላ ኢትዮጲያ ሰርገው በመግባት 182 ሰዎችን ገድለው 108 ሴቶች እና ህፃናቶችን አግተው ከወሰዱ ሁለት ሳምንት ሆነው ። ከጥቃት አድራሾቹ 60 መገደላቸውም ተነግረዋል ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:47

የታገቱት ህፃናት እና ሴቶች

ከጥቃት በኋላ የኢትዮጵያ መንግስት ሠራዊት ወደ ደቡብ ሱዳን በመግባት የታገቱት ህፃናት እና ሴቶች ያሉበትን እንደከበበም በዚያው ሰሞን ተነግሮ ነበር ።ይሁን እንጅ የኢትዮጵያና የደቡብ ሱዳን መንግስታት የታገቱትን ለማስለስ በጋራ እየሰሩ መሆኑ ከመገለጹ ውጭ ከሁለት ሳምንት በላይ የታገቱት ህፃናት በምን ሁኔታ ዉስጥ እንሚገኙ እስካሁኑ የተሰማ ነገር የለም ።ህፃናቱን ለማስለቀቅ በእትዮጲያ ሆነ በሱዳን በኩል የተጀመረው ጥረት ጥሩ ውጤት እንዳስገኘ በፌዴራል እና አርብቶ አደር ልማት ጉዳዮች ሚኒስትር የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ አበበ ወርቁን ይናገራሉ።

የኢትዮጵያ መንግስት ህፃናቱን የማስመለሱጉዳይ መጀመርያ በድርድር መፈታት እንዳለበት እና የታገቱት ደህንነታቸዉ ተጠብቆ መመለስ አለባቸዉ የሚል አቋም እንዳላዉ አቶ አበበ ይናገራሉ። አዝማምያዉም ጥሩ ደረጃ ላይ ቢሆንም ድርድሩ ግን ጊዜ እንደምወስደዉ ይናገራሉ። ይሁንና የታገቱትን ለማስለቀቅ መከላክያ ሠራዊት ቢላኪም በሁለት ሳምንት ውስጥ ምንም የተጨበጠ ነገር ላይ አለመደረሱ ማነጋገሩ ቀጥሏል።

በጉዳዩ ላይ በፌስቡክ ገፃችን ላይ በተካሄደ ውይይት አበዛኛዎቹ አስተያየት ሰጭዎች <<ጀግና የሚባለው መከላከያ ሰራዊታችን የት ገባ?>> የታገቱበትን ቦታ ለይተን አዉቀናል፣ ከበናል የተባለው ምን ላይ ደረሰ ብለዉ በጥያቄ መልክ መንግስትን ተችተዋል።


ይሁን እንጅ እንደ አቶ አበበ መንግስት ወቅታዊ እና በተከታታይ መረጃዎች እየሰጠ መሆኑን ይናገራሉ። ሌሎች አስተያየት ሰጭዎች የኢትዮጲያ መንግስት የታገቱት <<በረሀብና እንግልት>> ከመሞታቸዉ በፊት መንግስት ርምጃ መውሰድ እንዳለበት ያሳስባሉ ። የመንግስት ስረት አናሳ ነው ሲሉ የተቹም አሉ። በደቡብ ሱዳን መንግስት በኩል ምን እንደተደረገ እንደሆነ መረጃ ለማግኘት ያደርገነዉ ጥረት አልተሳካልንም።

መርጋ ዮናስ

ሒሩት መለሠ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች