አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ወደ ሀገር ቤት ገብቷል
ሰኞ፣ መስከረም 1 2010ማስታወቂያ
የመን በጦርነት ላይ ነች፡፡ የሳዑዲ አረቢያ መራሹ ጦር በየጊዜው የአየር ድብደባ ይፈጽመባታል፡፡ በሀገሪቱ የተዛመተው ወረርሽኝ ከግማሽ ሚሊዮን ህዝብ በላይ ለህመም መዳረጉ ተዘግቧል፡፡ እንዲህ አይነት ችግሮች በተደራረቡባት የመን ኢትዮጵያውያን የአዲስ ዓመት በዓልን እንዴት እያከበሩ ነው? ጥያቄው የቀረበለት የሰንአውን ወኪላችንን ግሩም ተክለ ሃይማኖት “ኢትዮጵያውያን ተሰባስበው በዓሉን ቢያከብሩም አከባበሩ ከበፊቱ በጣም ቀዝቅዟል” ይላል፡፡ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ወደ ሀገር መግባቱን የሚናገረው ግሩም በኢኮኖሚ ችግርም፣ በስራ ማጣትም “ቀዝቀዝ ብሎ ወዙ መፍዘዙ አልቀረም” ሲል በየመን ያለውን ሁኔታ ያስረዳል፡፡
ግሩም ተክለ ሃይማኖት
ተስፋለም ወልደየስ
ኂሩት መለሰ