በወቅታዊ ጉዳይ ላይ በሪያድ የኢትዮጵያዉያን አስተያየት | ኢትዮጵያ | DW | 21.10.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

በወቅታዊ ጉዳይ ላይ በሪያድ የኢትዮጵያዉያን አስተያየት

የኢትዮጵያ መንግሥት ያወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እና ዝርዝር መመሪያዎቹ ገዢው ፓርቲ ለበርካታ ዓመታት ሲተገብራቸው የኖሩትን ተግባራት ሕጋዊ ለማሰኘት ተብለው የወጡ እንጂ እንደ አዲስ ሊታዩ ይገባቸዋል ብለው እንደማያምኑ አስተያየታቸውን የሰጡ የሪያድ ነዋሪ ኢትዮጵያዊያን ገለጹ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:13

የኢትዮጵያዉያን አስተያየት

 እንደ አስተያየት ሰጪዎቹ እምነት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁም ሆነ የአፈጻጸም መመሪያው መንግሥት ያመጡልኛል ከሚላቸው መረጋጋቶች ይልቅ ማኅበራዊ መናጋቶችን፤ ከሰላም ይልቅ ቀውስን የሚጋብዙ ናቸው። እንደነሱም አዋጁ ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ እንደ ፓርቲም ሆነ እንደ መንግሥት ለዓመታት በመልካም ገጽታ ግንባታ በተለይም በዲፕሎማሲዉ መስክ አምጥቻቸዋለሁ በሚለው ስኬቶች ላይ ውኃ የመቸለስ ያህል ነው። ስለሺ ሽብሩ ከሪያድ   ተከታዩን ዘገባ አጠናቅሯል።

ስለሺ ሽብሩ

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic