በኦሮምያ የቀጠለው ተቃውሞ እና አንድምታው | ኢትዮጵያ | DW | 22.10.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

በኦሮምያ የቀጠለው ተቃውሞ እና አንድምታው

ሰልፎቹን በቅርበት የሚከታተሉ አስተያየት ሰጭዎች እንደሚሉት የቅርብ ጊዜዎቹ ሰልፎች ከቀደሙት በዓይነታቸው ይለያሉ። እንደ ቀደሙት ሰልፎች በውጭ ከሚኖሩ የኦሮሞ መብት ተሟጋቾች ድጋፍ የላቸውም የሚባሉት የነዚህ ሰልፎች ጠሪ አካል ማን እንደሆነ ግልጽ አይደለም፣ ከሚሉት አንስቶ ኦህዴድ ያደራጃቸው ሰልፎች ናቸው የሚሉ አስተያየቶችም ይሰማሉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 30:39

የኦሮምያ የተቃውሞ ሰልፍ እና አንድምታው

በኢትዮጵያ ለአንድ ዓመት ያህል የተደነገገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከተነሳ በኋላ ከአዋጁ በፊት እንደነበረው በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች የተቃውሞ ሰልፎች መካሄዳቸው ቀጥሏል። ጋብ እያሉ በበሚያገረሹት ሰልፎች የሚካፈለው ህዝብ ፖለቲካዊ ኤኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጥያቄዎች እየቀረቡ ነው። ከተማሪዎች በተጨማሪ የመንግሥት ሠራተኞች እንዲሁም የፀጥታ ኅይሎች ጭምር በሰልፎቹ ተሳታፊ መሆናቸው ይዘገባል።

ራስን የማስተዳደር መብት ይከበር ፣ የታሰሩ የኦሮሞ የፖለቲካ መሪዎች ይፈቱ የሚሉ እና የመሳሰሉ ጥያቄዎች ከሚነሱባቸው ሰልፎች በአንዳንዶቹ የኦሮምያ ርዕሰ መስተዳድር የኛ ናቸው የሚሉ መፈክሮችም ተደምጠውባቸዋል። ሰልፎቹ ወደ ረብሻ በተቀየሩባቸው አካባቢዎች በ10 የሚቆጠሩ ሰዎች መሞታቸው ተዘግቧል። አብዛኛዎቹ ግን በሰላም ተጀምረው በሰላም ማብቃታቸውን የዓይን ምስክሮች ለዶቼቬለ ተናግረዋል።

ሰልፎቹን በቅርበት የሚከታተሉ አስተያየት ሰጭዎች እንደሚሉት የቅርብ ጊዜዎቹ ሰልፎች ከቀደሙት በዓይነታቸው ይለያሉ። እንደ ቀደሙት ሰልፎች በውጭ ከሚኖሩ የኦሮሞ መብት ተሟጋቾች ድጋፍ የላቸውም የሚባሉት የነዚህ ሰልፎች ጠሪ አካል ማን እንደሆነ ግልጽ አይደለም፣ ከሚሉት አንስቶ የኦሮሞ ህዝቦች ዶሞክራሲያዊ ድርጅት ኦህዴድ ያደራጃቸው ሰልፎች ናቸው የሚሉ አስተያየቶችም ይሰማሉ። የኦሮሞ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት  የክልሉን የተሐድሶ አመራር የሚደግፍ በማስመሰል የሚካሄድ ነው ላለው ሰልፍ ተጠያቂዎቹ በአቋራጭ ለመበልፀግ የሚፈልጉ ኃይሎች ናቸው ብሏል። በኦሮምያ የቀጠለው ተቃውሞ እና አንድምታው የዛሬው እንወያይ ርዕስ ነው።ውይይቱን ለማዳመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ። 

ኂሩት መለሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

 

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች