በኦሮሚያ የተካሄደው የስራ ማቆም አድማ | ኢትዮጵያ | DW | 03.09.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

በኦሮሚያ የተካሄደው የስራ ማቆም አድማ

በኢትዮጵያ አስር ወራት ጸንቶ የቆየው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ  ባለፈው ሀምሌ 28 ፣ 2009 ዓም  ከተነሳ ከጥቂት ቀናት በኋላ ጀምሮ በብዙ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል አካባቢዎች የስራ ማቆም አድማ እና አልፎ አልፎ ያለመረጋጋት ታይቷል። የመጀመሪያው የስራ ማቆም አድማ አዋጁ ከተነሳ ከሁለት ሳምንት በኋላ በባህር ዳር ከተማ ነበር የተካሄደው።

ባለፈው ሳምንትም ከ2007 ዓም ወዲህ ተቃውሞ ባስተናገደው የኦሮሚያ ክልል ውስጥ፣ በብዙ አካባቢዎች ከነሀሴ 17 እስከ 21፣ 2009 ዓም በክልሉ የስራ ማቆም አድማ ተጠርቶ ነበር። ማንነታቸው ይፋ ያልተደረገ ከሀገር ውጭ እና ቄሮ በሚል መጠሪያ በሀገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ኃይላት በማኅበራዊ ደረ ገጾች የጠሩት የዚሁ የስራ ማቆሙ አድማ አስተባባሪዎች እንዳሉት፣  ለአምስት ቀናት ተጠርቶ የነበረው ይኸው የስራ ማቆም አድማ ያስቀመጣቸውን ዓላማዎች በማሳካቱ በሶስተኛው ቀን ፣ ነሀሴ 19፣ 2009 ዓም ተቋርጧል። በአድማው ሰበብ በብዙ የክልሉ አካባቢዎች የንግዱ እና የመጓጓዣው አገልግሎት ተቋርጦ ነበር፣ መንገዶች ተዘግተው እና ስራ ማቆም ባልፈለጉ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች አሽከርካሪዎች ላይም ጥቃት መጣሉ ተሰምቷል። በጅማ በአንድ የገበያ ቦታ ማንነታቸው ያልታወቁ ሰዎች በጣሉት የእጅ ቦምብ  ቢያንስ 13 ሰዎች ቆስለዋል።  የስራ ማቆሙ አድማ፣ ምክንያቱ  እና ዓላማው የዛሬው ውይይት ርዕስ ነው።  

አርያም ተክሌ

ልደት አበበ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች