1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኦሮሚያ ተባብሶ የቀጠለዉ ተቃዉሞ ምክንያትና መፍትሄዉ

ረቡዕ፣ የካቲት 23 2008

ኢትዮጵያ ዉስጥ በተለያዩ አካባቢዎች በአገሪቱ መንግሥት ላይ ተቃዉሞዎች እየተቀሰቀሱ ነዉ። ከዚህ ቀደም የወልቃይት ጠገዴ አካባቢ ነዋሪዎች ወደ አማራ ክልል እንጠቃለል በማለት ያነሱትን ጥያቄ አሁንም እንዳቀጠሉ ነዉ። ጋምቤላና ሲዳማ አካባቢም ተቃዉሞና ግጭት መቀስቀሱ ተዘግቧል።

https://p.dw.com/p/1I3g8
Oromo Proteste in Äthiopien
ምስል Oromia Media Network

[No title]

ከሁሉም አካባቢዎች የከፋዉ ግን በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የተለያዩ አካባቢዎች የሚታየዉ ተቃዉሞና ግጭት ነዉ። ከአንድ ዓመት ተኩል በኋላ በድጋሚ ያገረሸውና አራተኛ ወሩን ለያዘው ለዚህ ተቃዉሞ የሚሰጠዉ ምክንያት የተለያየ ነዉ። ከዚህ በፊት ተግባራዊ ይደረጋል የተባለዉ የአዲስ አበባና የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ የጋራ ማስተር ፕላን «ይሰረዝ» የሚለዉ ተቃዉሞ ከተነሳ በኋላ መንግሥት እቅዱን መሰረዙን ቢያስታዉቅም ተቃዉሞዉ ተባብሶ እንደቀጠለ ነዉ። በኦሮሚያ ክልል ዳግም ያገረሸዉ አመፅ እና ግጭት ተዋናይ ናቸዉ ባሏቸዉ ኃይሎች ላይ መንግሥት ሕጋዊና የማያዳግም እርምጃ እንደሚወስድ ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ አስታዉቀዋል። «ሂውመን ራይትስ ዎች» የተሰኘዉ የመብት ተሟጋች ድርጅት በኦሮሚያ የጭካኔ ግድያ እንዲቆም ሲል የጠየቀበት ዘገባዉን ያወጣዉ በዚሁ በያዝነዉ ሳምንት ነዉ። በኦሮሚያ ተባብሶ የቀጠለዉ ተቃዉሞ ምክንያትና መፍትሄዉ የዕለቱ የእንወያይ ዝግጅት ርዕስ ነዉ።

አዜብ ታደሰ

ልደት አበበ