በተቃዋሚዎች ላይ የተሰጠው ፍርድና የዶናልድ ፔይን አስተያየት | ኢትዮጵያ | DW | 13.06.2007
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

በተቃዋሚዎች ላይ የተሰጠው ፍርድና የዶናልድ ፔይን አስተያየት

የዩኤስ አሜሪካ የምክር ቤት እንደራሴና በምክር ቤቱ

የውጭ ግንኙነት ክፍል የዓለም የጤና ንዑስ ክፍል ኮሚቴ ሊቀመንበር ዶናልድ ፔይን እና የአውሮጳ ምክር ቤት አባል ወይዘሮ አና ጎሜሽ ትናንት አንድ የጋራ መግለጫ አወጡ። መግለጫው የኢትዮጵያ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሁለተኛ ወንጀል ችሎት በሠላሣ ስምንት የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች፡ በፓርላማ ተመራጮች የፖለቲካ መሪዎችና በጋዜጠኞች ላይ ያስተላለፈውን የጥፋተኝነት ውሳኔ አውግዞዋል። ውሳኔው የኢትዮጵያ የፍትህ ሥርዓት በገዢው ፓርቲ መዳፍ ሥር መውደቁን የሚያመላክት መሆኑንም መግለጫው አክሎ አስታውቋል። መግለጫውን መነሻ በማድረግ እንደራሴ ዶናልድ ፔይንን ያነጋገረው ወኪላችን አበበ ፈለቀ እንደራሴው ፍርድ ቤቱ ያሳለፈውን የጥፋተኝነት ውሳኔን ጠብቀውት እንደነበር ጠይቋቸዋል።