በርሊንና የዉድ ተሽከርካሪዎች መጋየት | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 17.08.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

በርሊንና የዉድ ተሽከርካሪዎች መጋየት

በርሊን ዉስጥ በአንድ ምሽት 17 ዉድ አዉቶሞቢሎች ሆን ተብሎ በእሳት መጋየታቸዉን ፖሊስ አመለከተ።

default

ትናንት ምሽት ከተፈጸመዉ ሌላ ቀደም ባለዉ ቀንም እንዲሁ 18 መኪኖች በተመሳሳይ መንገድ መንደዳቸዉ ተገልጿል። ድርጊቱ የተፈጸመዉ በሃብታሞች መኖሪያ አካባቢ መሆኑን ያመለከተዉ የፖሊስ መረጃ ወንጀሉ የተፈጸመዉ ምናልባት በናጠጡ ሃብታሞችና ተቋሞች ላይ ተቃሞዉ ያላቸዉ የግራ ጽንፈኞች ያደረጉት ሊሆን እንደሚችል ግምቱን ሰንዝሯል። ምናልባትም ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ አፍላ ታዳጊ ወጣቶች ድርጊትም ሊሆን እንደሚችልም ተገምቷል። የአዉቶሞቢል ቃጠሎዉ የትናንት እና ከትናንት በስተያ ብቻ እንዳልሆነ ነዉ የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለሚካኤል የሚያስረዳዉ።

ይልማ ኃይለሚካኤል

ሸዋዬ ለገሠ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic