በሊብያ ያሉ ኤርትራውያን ስደተኞች የገጠማቸው ችግር | ኢትዮጵያ | DW | 13.07.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

በሊብያ ያሉ ኤርትራውያን ስደተኞች የገጠማቸው ችግር

በሊብያ በስደት የሚገኙ ኤርትራውያን በትልቅ ስቃይ ላይ መሆናቸውን ለስደተኞች መብት የሚሟገተው በብራስልስ የሚገኘው የአውሮጳ የስደተኞች ምክር ቤት እና የኢጣልያ አጋሩ፡ እንዲሁም፡ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል ሰሞኑን በጋራ አስታወቁ።

default

ድርጅቶቹ እንዳስረዱት፡ የሊብያ የጸጥታ ኃይላት ሁለት መቶ የሚሆኑ ኤርትራውያን ስደተኞችን ሚስራታህ ከሚባለው የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ በግዳጅ በረሃማ ወደሆነው ወደ ብራክ መጠለያ ጣቢያ አዛውረዋቸዋል። ስደተኞቹ በዚያ እንግልት ስለደረሰባቸውም አስቸኳይ ርዳታ እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል። ወደ ኤርትራ ቢመለሱ የመታሰር እና የመሰቃየት ዕጣ ሊገጥማቸው ስለሚችል፡ የሊብያ መንግስት ስደተኞቹን በግዳጅ ወደ ሀገራቸው እንዳይመልስ የአውሮጳ ህብረት የሚቻለውን እንዲያደርግ ድርጅቶቹ በተጨማሪ ጠይቀዋል።

ገበያው ንጉሴ

አርያም ተክሌ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች