በሊቢያ አቀባበል የብሪታኒያ ቁጣ | ዓለም | DW | 21.08.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

በሊቢያ አቀባበል የብሪታኒያ ቁጣ

ከሀያ አንድ ዓመት በፊት ሎከርቢ ሰማይ ላይ በፈነዳው የፓን አሜሪካን አውሮፕላን ለጠፋው የሰው ህይወትና ንብረት በጥፋተኝነት ተወንጅሎ የዕድሜ ልክ እዕስራት የተፈረደበት ሊቢያዊው አቤል ቤሴት አል ሜግራሂ ትናንት ተለቆ ወደ ሀገሩ ሲገባ የተደረገለት የጀግና አቀባበል ተደረገለት።

default

ትሪፖሊ አዉሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ

ይህ አቀባበል የብሪታኒያን መንግስትና አሜሪካንን አስቆጥቷል። የብሪታኒያ ውጭ ጉዳዪ ሚኒስትር ዴቪድ ሚሊባንድ አቀባበሉን በጣም የሚያበሳጭ ብለውታል ። አቤሌ ቤሴት ትናንት ትሪፖሊ ሲገባ በርካታ ህዝብ የተቀበለው ሲሆን ከአውሮፕላኑ በሚወርድበት ጊዜም አንዳንዶች አባባ በመበተን ነበር የተቀበሉት ። ሀና ደምሴ ዝርዝር አላት

ሀና ደምሴ ፣ ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ