ቅድመ ምርጫ ብጥብጥ በግብፅ | አፍሪቃ | DW | 26.04.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

ቅድመ ምርጫ ብጥብጥ በግብፅ

ሥልጣን ከጨበጠ ከ 1 ዓመት በላይ ያስቆጠረው የግብፅ ከፍተኛ ወታደራዊ ምክር ቤት በአሁኑ ሰዓት ሁሉንም ግብፃውያን ያስቆጣ ይመስላል ። የቀድሞዎቹ ምሁራን አሁንም የግብፅ እጣ ፈንታ ወሳኞች መሆናቸው በተለይ ወጣት አብዮተኞቹን አበሳጭቷል ።

 በእድሜ የገፉትም ቢሆኑ ደስተኛ አይደሉም ። ድምፃቸውን የማያሰሙት ብዙሃኑ ግብፃውያን ደግሞ ወራት ካስቆጠረው ብጥብጥ በኋላ አምባገነንም ቢሆን ተቀባይነት ያለው  መሪ እንደሚፈልጉ አንድ ጥናት አመልክቷል ። የሙስሊም ወንድማማቾች ማህበርና ና የሳላፊዎች  ቡድንም እንዲሁ በወታደራዊው ምክር ቤት ላይ ተቀወሞአቸውን እያሰሙ ነው ። Anne Allmeling ያቀረበችውን ዘገባ ሂሩት መለሠ አጠናቅራዋለች ።

አን አልሜሊንግ

ሂሩት መለሠ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic