ስፖርት ፤ ታህሳስ 4 ቀን፣ 2008 ዓ.ም | ስፖርት | DW | 15.12.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ስፖርት

ስፖርት ፤ ታህሳስ 4 ቀን፣ 2008 ዓ.ም

በፈረንሳይ በሚደረገዉ አገር አቋራጭ አትሌቲክስ ዉድድር የጀርመን አትሌቲክስ ቡድን በአራት አጠቃላይ ሜዳሊያ ሦስተኛ ደረጃን ይዞአል።

በፈረንሳይ በተካሂደው የ 2015 የአውሮጳ አገር አቆዋራጭ የአትሌቲክስ ውድድር የእንግሊዝ አትሌቲክስ ቡድን በአገኘው አጠቃላይ 9 ሚዳልያ ቀዳሚ ሲሆን የስፔን አትሌቲክስ ቡድን በ 6 ሜዳልያዎች ሁለትኛ የጀርመን አትሌቲክስ ቡድን ደግሞ 4 ሚዳልያ በማግኘት ሶስትኛ ደረጃን ይዞአል።

በእንግሊዝ የባርክ ሌይ ፕርሚየር ሌግ አስራ ስድስተኛ ሳምንት የእግር ኳዋስ ጨዋታ አሁንም ለትንበያ አስቸጋሪ መሆኑን ቀጥልዋል ቅዳሚ ትንሹ ቦርንማውዝ ግዙፉ ማንችስተር ዮናይትድን ሁለት ለአንድ አሸንፎዋል። ክርስታል ፓላ ሳውዝ ሀምፕተንን፣ ዋትፈርድ ሰንደርላንድን አንድለ ባዶ በሆነ ተመሳሰይ ውጤት ሲያሸንፉ፣ ማንችስተር ሲቲ ስዋንዚን ሁለት ለአንድ ረትዋል እሁድ አርሰናል አስቶቪለን ሁለት ለበዶ ረትዋል ማክሰኞ ታጅሳስ 5 ሌስተር ሲቲ ከቸልሲ የጫወታል።

የእንግሊዝን ፕርሜየር ሊግ አርሰናል ለጊዚው በ 33 ነጥብ አንደኛ ሆኖ ሲመራው አንድ ተስተካካው ጨዋታ የሚቀረው ሌስትር ሲቲና ማንችስተር ሲቲ 32 ነጥብ ሁለትኛ እና ሶስተኛ ሆነው ይከተለሉ። ማንችስተር ዩናይትድ 29 ነጥ 4 ደረጃ ላይ የገኛል። ኖርዊች ሰንደርለንድ እና አስቶንቬላ 18 19 20 ኛ ላይ ናቸው ።

በጀርመን ቡንዲስሊጋ

አጉስበርግ ሻልካን ሁለት ለዜሮ ዶርቱ መንድ ፍራንክፈርትን አራት ለአንድ ረተዋል ባየር ሙኒክ ኢንጉሽታድን ሁለት ለዜሮ አሸንፎዋል። በጀርመን ቡንዲስ ሊጋ ባየር ሙኒክ በ 43 ነጥብ ሲመራ ቦሬስያ ዶርቱ መንድ በ 38 ነጥብ ሁለተኛ ሆኖ ይከተላል። ሃርታ በርሌን በ 29 ነጥብ ሶስታኛ ሲሆን ቮልፍስበርግ 26 ነጥብ ይዞ አራተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ሀኖቨር ሆፍንሀም እና ሽቱትጋርት በወራጅ ቀጠና የተቀመጡ ናቸው።

ሀና ደምሴ

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic