የኢጣልያ መንግሥት ብዙዎች ከአፍሪቃ ወደ አውሮጳ የሚሰደዱበትን ድርጊት ለማከላከል በጀመረው ጥረቱ ለሶስት የአፍሪቃ ሃገራት 200 ሚልዮን ዩሮ ድጋፍ አደረገ። ስደተኞችን በዚያው በአፍሪቃ ለማስቀረት የታስቦ የተደረገውን የገንዘብ ድጋፍ የሚያገኙት ስደተኞች በተለይ በመሸጋገሪያነት የሚጠቀሙባቸው ሊቢያ፣ ኒጀር እና ቱኒዝያ ናቸው።
ተኽልእዝጊ ገብረየሱስ
አርያም ተክሌ
ስደተኞች የሜዴትራንያንን ባህር አቋርጠው ወደ አውሮጳ እንዳይገቡ የህብረቱ የባህር ድንበር ጠባቂ ፍሮንቴክስ ጥበቃውን አጠናክሯል። በህገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ላይም ዘመቻ እየተካሄደ ነው። ኢጣልያ የምትረዳቸው የሊቢያ የፀጥታ ኃይላት ስደተኞችን አሳፍረው ወደ አውሮጳ ለመሄድ የሚሞክሩ ጀልባዎችን ወደ ሊቢያ እየመለሱ ነው።
ከሁለት ዓመት በፊት የአፍሪቃ እና የአዉሮጳ መንግሥታት መሪዎች ማልታ ላይ ተሰባስበዉ ነበር። ከትናንት ጀምረዉ ደግሞ አቢዦን ኮትዴቩዋር ተገናኝተዋል። ከማልታዉ ንግግር በኋላ የደረሱባቸዉን አንዳንድ የስምምነት ነጥቦች በሥራ ላይም አዉለዋል።
አፍሪቃ ዉስጥ በቀጣይ 80 ዓመታት አሁን ካለዉ የሕዝብ ብዛት በአራት እጥፍ የሚበልጥ ሕዝብ እንደሚኖር ከወዲሁ የሚወጡ ጥናቶች ይጠቁማሉ። በዚህ ወቅትም በተለይ ወጣቶች የወደፊት ሕይወታቸዉ ተስፋ እንዲኖረዉ ትምህርት እንደሚያስፈልጋቸዉ ይታመናል። የአዉሮጳ ኅብረት አፍሪቃ ዉስጥ ተገቢዉን ትምህርት በማስፋፋት የተሰዳጁን ቁጥር ለመቀነስ አልሟል።