ሳዲቅ ካን የመጀመሪያው ሙስሊም የለንደን ከንቲባ | ዓለም | DW | 09.05.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

ሳዲቅ ካን የመጀመሪያው ሙስሊም የለንደን ከንቲባ

ሙስሊሙ የሌበር ፓርቲ አባል ሳዲቅ ክሃን እንዳይመረጡ ከተቀናቃኞቻቸው በተለይም ከወግ አጥባቂ ፓርቲ አመራርና አባላት ዘንድ ከፍተኛ የስም ማጥፋት ዘመቻ ሲካሄድባቸው ቆይቷል ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:10

ሳዲቅ ካህንባለፈው ሀሙስ ለለንደን ከንቲባነት በተካሄደ ምርጫ ያሸነፉት የመጀመሪያው ሙስሊም ከንቲባ ርሳቸውና ቤተሰባቸው ያገኙትን እድል ሁሉም የለንደን ነዋሪ እንዲያገኝ እንደሚሹ አስታወቁ ። ከፓኪስታን ስደተኛ ቤተሰብ ለንደን ተወልደው ያደጉት ሙስሊሙ የሌበር ፓርቲ አባል ሳዲቅ ን እንዳይመረጡ ከተቀናቃኞቻቸው በተለይም ከወግ አጥባቂ ፓርቲ አመራርና አባላት ዘንድ ከፍተኛ የስም ማጥፋት ዘመቻ ሲካሄድባቸው ቆይቷል። የለንደኑ ወኪላችን እንደዘገበው ይህ በዘርና በሃይማኖት ላይ ያተኮረው ዘመቻ ቅሬታን አስከትሏል ።

ድልነሳ ጌታነህ

ኂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic