ሳዑዲ አረቢያ ግጭትና የእስረኞች ማምለጥ | ኢትዮጵያ | DW | 30.09.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ሳዑዲ አረቢያ ግጭትና የእስረኞች ማምለጥ

በርካታ እስረኞች ቆሰሉ።ቁጥራቸዉ በዉል ያልታወቀ ደግሞ ከማቆያ ጣቢያዉ አመለጡ።በግጭት-ረብሻዉ ከኢትዮጵያ ሌላ የናይጄሪያ፥ የሶማሊያ፥ እና የየመን ዜጎችም አሉበት ተብሏል።

default

ስደት

ጂዳ-ሳዑዲ አረቢያ ማቆያ ጣቢያ ዉስጥ በታሰሩ ኢትዮጵያዉያን ስደተኞችና በፀጥታ አስከባሪዎች መካከል ትናንት በተነሳ ግጭት በርካታ እስረኞች ቆሰሉ።ቁጥራቸዉ በዉል ያልታወቀ ደግሞ ከማቆያ ጣቢያዉ አመለጡ።በግጭት-ረብሻዉ ከኢትዮጵያ ሌላ የናይጄሪያ፥ የሶማሊያ፥ እና የየመን ዜጎችም አሉበት ተብሏል።የሳዑዲ አረቢያ የፓስፖርት ጉዳይ መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ እንዳስታወቀዉ እስረኞቹ ያለ ሕጋዊ ፍቃድ ሳዑዲ አረቢያ በመኖራቸዉ የተያዙ እንጂ ከፍተኛ ወንጀል የፈፀሙ አይደሉም።በቃል አቀባዩ መግለጫ መሠረት እስረኞቹ ያመለጡት ወደየመጡበት ሐገር ሊመለሱ ዝግጅት በሚደረግበት ወቅት ነዉ።የጂዳዉ ወኪላችን ነቢዩ ሲራክ ጉዳዩ ተከታትሎታል።

ነብዩ ሲራክ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች