ረሐብ በኢትዮጵያ ምክንያቱና መፍትሔዉ ክፍል II | ኢትዮጵያ | DW | 28.08.2008
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ረሐብ በኢትዮጵያ ምክንያቱና መፍትሔዉ ክፍል II

አሕያ መጣች ተጭና ምስር፣ እናትዬዋ ሞታለች ከሥር፣ ልጁ ይጠባል የረጋ ደም ሥር

default

ረሐብተኛ

ግማሽ ሚሊዮን ያክል ኢትዮጵያዊ መግደሉ ከሚገመተዉ ከ1977ቱ ረሐብ የተረፈዉ ፣-አሕያ መጣች ተጭና ምስር፣ እናትዬዋ ሞታለች ከሥር፣ ልጁ ይጠባል የረጋ ደም ሥር እያለ፣ ረሐብ ሥለገደላት ብጤዉ፣ መኖር-መዳኑ ስለማይታወቀዉ የረሐብተኛ ሞት ረሐብተኛ ልጅ አረዳ።የሰባ-ሰባቱ ሕፃን ሰማንያ ሰባት ለመራብ መድረስ አለመድረሱ እንደማይታወቅ ሁሉ የሰባ-ሰባቱ አርጂ በ1966ቱ ረሐብ ከሰባ-ሰባቱ ሕፃን መለየት-አለመለየቱም አይታወቅም።አንድ ነገር ግን ይታወቃል።ኢትዮጵያ የተራበ ዜጋዋ ቀድሞት ሥለተራበ ታላቁ፣ ረሐብ ሥለገደለዉ አቻዉ፣ ረሐብ ሥለሚጠብቀዉ ታናሹ እንደተናገረባት ስልሳ-ሰባ ዘመን እንደቆጠረችአለች።ዘንድሮም -አስር ሚሊዮን ረሐብተኛ ይቆጠርባታል።ጤና ይስጥልኝ እንደምን ዋላችሁ።ዘመን-ረሐብተኛዉን እየቆጠርን ስለማይልቀዉ ታሪክ ሳምንት የጀመርነዉን ዛሬ እንጨርሰዉ።