ሞሮኮ እና የአፍሪቃ ሕብረት | አፍሪቃ | DW | 28.10.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

   ሞሮኮ እና የአፍሪቃ ሕብረት

ንጉሡ መሐመድ VIኛ በይፋ ከተነገረዉ በላይ ከፍ ያለ አላማም አላቸዉ። ሃገራቸዉ ከሰላሳ-ዓመት በፊት የተለየችዉን ያሁኑን የአፍሪቃ ኅብረት ዳግም የተቀላቀለችበት ወቅት ነዉ። ሃገራቸዉ ኅብረቱን ዳግም እንደምትቀየጥ ንጉሡ ባለፈዉ ሐምሌ ለኅብረቱ በጻፉት ደብዳቤ አስታዉቀዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:16

ሞሮኮና የአፍሪቃ ሕብረት

የሞሮኮዉ ንጉሥ መሐመድ VI በሰወስት የአፍሪቃ ሃገራት የሚደርጉትን ይፋ ጉብኝት እንደቀጠሉ ነዉ። ካለፈዉ ሳምንት ጀምረዉ ሩዋንዳ፤ ታንዛኒያንና ኢትዮጵያን እየጎበኙ ነዉ። በአዲስ አበባ ቆይታቸዉ ከኢትዮጵያ እና ከአፍሪቃ ኅብረት ባለሥልጣናት ጋር ይወያያሉ። ንጉሡ በተለይ ከአፍሪቃ ኅብረት ባለሥልጣናት ጋር በሚያደርጉት ዉይይት ኅብረቱን እንደ-አዲስ የተቀላቀለችዉ ሃገራቸዉ ከኅብረቱ ጋር ያላትን ግንኙነት በምታጠናክርበት ሥልት ላይ ትኩረት ሰጥተዉ ይነጋገራሉ፤ ዉሎችንም ይፈራረማሉ። ፊሊፕ ዛንድነር የዘገበዉን ነጋሽ መሐመድ አጠናቅሮታል።
የሩዋንዳ እና የታንዛኒያ መሪዎች አዲስ እንግዳቸዉን ለማስተናገድ ጠብ-እርግፍ ሲሉ ነዉ የሰነበቱት። በተለይ ደር ኤ ሠላሞች፤ ፊሊፕ ዛንድነር እንዘገበዉ ለንጉሡ ክብር የቆጠቡት የለም። የመድፍ ተኩስ፤  የክብር ዘብ ሰልፍ፤ ባሕላዊ ሙዚቃና ዳንኪራ፤ በስተማሳረጊያዉ የንጎሮንጎ ብሔራዊ ፓርክ ጉብኝት-ምንቀረ?
የጉብኝቱ ይፋ አላማ ሰሜን አፍሪቃዊቱ አረባዊት ሀገር ከሁለቱ የምሥራቅ አፍሪቃ ሃገራት ጋር ያላትን ፖለቲካዊ እና ምጣኔ ሐብታዊ ግንኙነትን ማጠናከር የሚል ነዉ። በልማዱ ምሥራቅ አፍሪቃዉያኑ ሃገራት ከሞሮኮ ጋር ብዙም ግንኙነት የላቸዉም። አሁን ግን የሞሮኮ መልዕክተኞች ከሩዋንዳ ጋር ብቻ

አስራ-ዘጠኝ ስምምነቶችን ተፈራርመዋል።
ንጉሡ መሐመድ VIኛ በይፋ ከተነገረዉ በላይ ከፍ ያለ አላማም አላቸዉ። ሃገራቸዉ ከሰላሳ-ዓመት በፊት የተለየችዉን ያሁኑን የአፍሪቃ ኅብረት ዳግም የተቀላቀለችበት ወቅት ነዉ። ሃገራቸዉ ኅብረቱን ዳግም እንደምትቀየጥ ንጉሡ ባለፈዉ ሐምሌ ለኅብረቱ በጻፉት ደብዳቤ አስታዉቀዋል።

አባታቸዉ ዳግማዊ ንጉሡ ሐሰን የቀድሞዉን የአፍሪቃ አንድነት ድርጅትን አልፈልግም ብለዉ የወጡት ድርጅቱ ለምዕራባዊ ሠሐራ ዕዉቅና በመስጠቱ ነበር። አሁን ግን፤- የአፍሪቃ ኅብረት ጉዳይ አጥኚ ሊስል ሎዉ-ቫዉድራን እንደሚሉት ሞሮኮዎች ከኅብረቱ መራቁ ብዙም እንደማይጠቅማቸዉ ተረድተዉታል።
                               
«የሞሮኮ ዲፕሎማቶች እንደሚሉት፤ በኅብረቱ አባል ሳይኮን ምዕራባዊ ሠሐራ የሞሮኮ ግማደ-ግዛት እንደሆነች የራስ-ገዝ መስተዳድር መብት ይኑራት የሚለዉን  የራባት አቋም ሌሎች የአፍሪቃ ሃገራት እንዲቀበሉት ማድረግ አይቻልም።»
የቀድሞዋን የስጳኝ ቅኝ ግዛት የምዕራባዊ ሰሐራን አብዛኛ ክፍል ሞሮኮ ከጠቀለለችዉ ከ40 ዓመት በልጦታል። ሌላዉን ክፍል የሚቆጣጠረዉ ፖሊሳርዮ-የተሰኘዉ ደፈጣ ተዋጊ ቡድን «ሠሐራዊ አረብ ሪፐብሊክ» የሚል ስም ሰጥቶታል። ቡድኑ የአፍሪቃ ኅብረት አባልም ነዉ። የግዛቲቱ የወደፊት ዕጣ ፈንታ በሕዝበ-ዉሳኔ እንዲበየን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ወስኗል።
ሞሮኮ ሕዝበ ዉሳኔዉ ከራስ-ገዝ አስተዳደር እርቆ የነፃነት ሐሳብን ማካተት የለበትም ባይ ናት። ወደ አፍሪቃ ኅብረት የተመለሰችዉም የኅብረቱ አባል ሃገራትን ድጋፍ ለማግኘት ይሕ ቢቀር ተቃዉሞዉን ለማስቀረት ነዉ። የራባት ገዢዎች ምዕራብ አፍሪቃዎችን ማግባባቱ ብዙ አልገደዳቸዉም።
ከምሥራቅ አፍሪቃ ደግሞ አሁን ተዘዋዋሪ ድጋፉ እየጎረፈላቸዉ ነዉ። የሩዋንዳዋ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ሉዊሴ ሙሺኪዋቡ ሞሮኮ ዳግም የአፍሪቃ ኅብረትን መቀየጧን «ተገቢና ወቅታዊ ብለዉታል።» የታንዛኒያዉ አቻቸዉ አዉጉስቲን ማሒጋ አጠናከሩት፤-
                             
«ለረጅም ጊዜ የአፍሪቃ ኅብረት አባል ባለመሆናቸዉ ድምፃቸዉ እንዲሰማ አንዳድ የአፍሪቃ ሃገራትን መምከሩ ጥሩ ነዉ የሚሉ አሉ። ይሕን ማለታቸዉ የሕጋዊ አባልነትን ሥራዓትን ይጠብቁ ማለታቸዉ ከሆነ

ብዙ የሚያስደንቅ አይሆንም። አሁን ግን ተመልከቱ፤ ከአቻዎችን አንዷናት የመጣችዉ።»

ሞሮኮ ዳግም አባልነቱን በጠየቀችበት ዕለት፤ ሰሐራዊት አረብ ሪፐብሊክ ከኅብረቱ እድትወጣ 28 የአፍሪቃ ሃገራት በደብዳቤ ጠይቀዉ ነበር። ይሁንና በአፍሪቃ ኅብረት ሕግ-መሠረት አባላት ከኅብረቱ የሚታገዱት በአባል ሀገሩ መፈንቅለ መንግሥት ሲደረግ ብቻ ነዉ። በዚያ ላይ ሰሐራዊት አረብ ሪፐብሊክ አሁንም ድረስ አልጄሪያ እና ደቡብ አፍሪቃን ከመሳሰሉ የኅብረቱ ከበድ ሚዛን አባላት ጠንካራ ድጋፍ ታገኛለች። በዚሕም ምክንያት የአፍሪቃ ሕግ ካልተቀየረ በስተቀር የሞሮኮ አባልነት ይፀድቃል እንጂ የሠሐራዊ አረብ ሪፐብሊክ አባልነት አይሰረዝም። ራባቶችም ለጊዜዉ ከዚሕ በላይ የሚፈልጉ አይመስሉም።

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ


 


 

 

Audios and videos on the topic