ምርምርና የተፈጥሮ ሃብት | ጤና እና አካባቢ | DW | 14.07.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ጤና እና አካባቢ

ምርምርና የተፈጥሮ ሃብት

ተፈጥሮ በአካባቢያችን የለገሰችንን ፀጋዎች መርምሮ ማወቁ፤ አዉቆም መጠበቁ ለጊዜዉ ብቻ ሳይሆን በዘላቂነት ያሉንን እየተጠቀሙ ለማኖር እንደሚረዳ ይታመናል።

default

በኢትዮጵያ በበርካታ እፅዋት ላይ ጥናት ያደረጉት ባለሙያ እንዲህ ያለዉ ዘመናዊ ምርምር ከኅብረተሰቡ እዉቀት እንደሚነሳ ይናገራሉ። ላለፉት 30ዓመታት በመማር፤ በማስተማርና በምርምር ዘርፍ እንደቆዩ የገለፁልን ባለሙያ ለፕሮፌሰርነት ያበቋቸዉ ስራዎች በርካታ ቢሆኑም በተለይ ሃለኮ ወይም ሽፈራዉ የተባለዉ ተክል ላይ ያካሄዱት ምርምርና የተባይ ማጥፊያ መድሃኒቶች በሰዎች ጤና ላይ ስለሚስከትሉት ችግር ዘርዝረዉ ለህትመት ያበቋቸዉ ግንባር ቀደሞቹ እንደሆኑ አስረድተዉናል።

ሸዋዬ ለገሠ