ማወዛገብ የቀጠለው የኬንያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ | አፍሪቃ | DW | 05.09.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

ማወዛገብ የቀጠለው የኬንያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ

በኬንያ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ የተወዳደሩት የተቃዋሚው ቡድን እጩ ራይላ ኦዲንጋ የሀገሪቱ አስመራጭ ኮሚሽን ጥቅምት 7 ቀን 2010 ዓ.ም ድጋሚ እንዲደረግ በወሰነው ፕሬዚደንታዊው ምርጫ ላይ ሕጋዊ እና ሕገ መንግሥታዊ ዋስትና ካላገኙ እንደማይሳተፉ አስታወቁ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 05:02

ኦዲንጋ በድጋሚ ምርጫ «ላልሳተፍ እችላለሁ» እያሉ ነው

አዲንጋ እና የተቃዋሚ ፓርቲዎች የምርጫው ዕለትም እንዲቀየር ከመጠየቃቸው ጎን እስከምርጫው ዕለት ይሟሉ ያሏቸው በርካታ ጥያቄዎች ማቅረባቸው ተሰምቷል።

የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በ60 ቀናት ውስጥ ድጋሚ ምርጫ እንዲካሄድ ባለፈው ዓርብ መወሰኑን ተከትሎ የሀገሪቱ የምርጫ እና ድንበር ኮሚሽን የድምጽ መስጫው ቀን ጥቅምት 7 ቀን 2010 ዓ.ም እንዲሆን ትላንት ውሳኔ አሳልፎ ነበር፡፡ ኦዲንጋ ዛሬ በሰጡት መግለጫ የምርጫው ዕለት በጥቅምት 14 አሊያም በጥቅምት 21 እንዲካሄድ እንደሚፈልጉ ገልጸዋል፡፡ በድጋሚ ምርጫው ለመሳተፍ መሟላት አለባቸው ያሏቸውን ቅድመ ሁኔታዎችም ዘርዝረዋል፡፡ ከቅድመ ሁኔታዎቹ ውስጥም የኬንያ ምርጫ ኮሚሽን ስድስት ኃላፊዎች ከስልጣናቸው እንዲነሱ የጠየቁበት ይገኛል፡፡

በኬንያ ድጋሚ ይደረጋል የተባለው ፕሬዚደንታዊ ምርጫን በተመለከተ የተቃዋሚው ወገን ስለያዘው አቋም ናይሮቢ የሚገኙትን የፖለቲካ ተንታኝ አቶ ፍቅረማርያም መኮንንን አነጋግረናቸዋል።

አርያም ተክሌ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች