ማሊ እና የምክር ቤታዊው ምርጫ ዝግጅት | አፍሪቃ | DW | 09.11.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

ማሊ እና የምክር ቤታዊው ምርጫ ዝግጅት

ምዕራብ አፍሪቃዊቱ ሀገር ማሊ እአአ የፊታችን ህዳር 24 አዲስ ምክር ቤት ትመርጣለች። የምርጫው ዘመቻ በሳምንቱ መጀመሪያ የተጀመረ ሲሆን፣ ለ147 የብሔራዊ ምክር ቤት መንበሮች 1141 ዕጩዎች በተወዳዳሪነት ቀርበዋል።

ተመራጮቹ እንደራሴዎች በምክር ቤት ቦታቸውን የሚይዙበት ድርጊት ከሦስትወር በፊት ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ያካሄደችው ማሊ ያነቃቃችውን አዲስ ጅምር ወደፊት የሚያራምድ ሌላ ርምጃ ሆኖ ታይቶዋል።

ወደ 6,5 ሚልዮን የሚጠጉት የመምረጥ መብት ያላቸው የማሊ ዜጎች ከሁለት ሳምንት በኋላ ይመረጣል የሚባለው አዲሱ ምክር ሀገራቸውን ከምትገኝበት ቀውስ ለማላቀቅ ድርሻ ያበረክታል በሚል ተስፋ አድርገዋል። ከአንድ ዓመት ተኩል በፊት፣ እአአ መጋቢት 21፣ 2012 ዓም የጦር ኃይሉ በመፈንቅለ መንግሥት የቀድሞውን የማሊ ፕሬዚደንት አማዱ ቱማኒ ቱሬ ከሥልጣን ባስወገደበት እና በሰሜናዊ የሀገሪቱ አካባቢ ከሚንቀሳቀሱት የቱዋሬግ ዓማፅያን ጋ ጦርነት በተካሄደበት ጊዜ ነበር ቀውሱ የተጀመረው። ያማፀያኑ እንቅስቃሴ በውጭ ጦር ጣልቃ ገብነት በተገታበት ጊዜ ባካባቢው የፈጠረው እፎይታ በምርጫው እንደሚጠናከር የሀገሪቱ ሕዝብ ተሰፋ ማድረጉን በማሊ መዲና ባማኮ የሚገኘው «ብሔራዊ ዴሞክራቲክ ተቋም» የተባለው ያሜሪካውያኑ የፖለቲካ ጥናት ድርጅት ባልደረባ ባዲየ ሂማ ገልጸዋል።

ARCHIV - Ex-Ministerpräsident von Mali Ibrahim Boubacar Keita spricht zu seinen Unterstützern in seinem Hauptquartier in Bamako, Mali am 04.05.2013. Am 11.08.2013 findet die Stichwahl zwischen Boubacar Keïta und Ex-Finanzminister Cissé statt. Foto: EPA/TANYA BINDRA +++(c) dpa - Bildfunk+++

ፕሬዚደንት ቡባከር ኬይታ

« የማሊ ዜጎች ምክር ቤታዊው ምርጫ በሀገሪቱ እንደገና መረጋጋት እና ሥርዓተ ዴሞክራሲን ያስገኛል በሚል ትልቅ ተስፋ ያሳደሩ ይመስለኛል። »

ጽሕፈት ቤቱን በማሊ የከፈተው የጀርመናውያኑ የ«ፍሪድሪኽ ኤበርት ተቋም» ባለደረባ አኔተ ሎማንም ቀጣዩ ምክር ቤታዊ ምርጫ ያለፈው አንድ ዓመት ተኩልን ውዝግብ ባዳቀቃት ማሊ ውስጥ አዲስ የፖለቲካ ጅምር እንዲነቃቃ ሁኔታዎችን የሚያመቻች ርምጃ መሆኑን አስታውቀዋል፤ ግን ከብዙዎቹ ርምጃዎች መካከል አንዱ ብቻ መሆኑን ነው ያጎሉት።

« የፍትሑ ጉዳይ እንዴት ነው? በማሊ ሀቀኛውን ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመገንባት ከተፈለገ ቀጣዩ ርማጃ ነፃና ገለልተኛ የሆነ የፍትሕ አውታር መትከል ነው። እርግጥ፣ በሀገሪቱ ገና ብዙ መሰራት አለበት። ይሁንና፣ ምክር ቤቱ ዋነኛው እና ማዕከላዩ የፖለቲካ ሚና ይዞዋል። በመሆኑም፣ በሀገሪቱ ሥልጣን ክፍፍል እና ቁጥጥርን በተመለከተም ወደፊት ብዙ ማበርከት ይጠበቅበታል። »

FILE - In this Friday, July 26, 2013 file photo, rebels from the National Movement for the Liberation of the Azawad (NMLA) stand guard outside the former governor's office, in Kidal, Mali. Malian soldiers and ethnic Tuareg separatist rebels clashed again in the northern desert town of Kidal early Monday, Sept. 30, 2013, a day after trading gunfire downtown in a battle that has raised fears about whether an unraveling peace accord could lead to protracted fighting in the region. (AP Photo/Rebecca Blackwell, File)

የቱዋሬግ ዓማፅያን

ምክንያቱም ባለፉት ጊዚያት የሀገሪቱ ምክር ቤት ደካማ ነበር፤ በነበረውን ሥልጣን ተጠቅሞ መንግሥቱን በመቆጣጠር ወይም ሀገሪቱን የሚጠቅም የሕግ ረቂቅ በማውጣት ፈንታ፣ መንግሥት ያቀርብለት የነበሩትን የሕግ ረቂቆች ብቻ ካላንዳች ክርክር ነበር ያሳለፈው። የቀድሞው ፕሬዚደንት ይከተሉት የነበረው ተግባብቶ የመስራት ፖለቲካ ፣ ማለትም፣ የተቃዋሚው ቡድን ከመንግሥት ጋ ግንኙነት በመፍጠሩ፣ በሀገሪቱ የመድብለ ፓርቲ ሥርዓት እንዳይቋቋም አከላክሎ ነበር። ይህ ዓይነቱ ሁኔታ አሁንም የሚደገምበት አዝማሚያ መታየቱን አኔተ ሎማን ጠቁመዋል።

« በአሁኑ ጊዜ ሁሉም ፓርቲዎች እና ዕጩዎች ራሳቸው ለማስተዋወቅ፣ አንዱ ከሌላው ጋ ጥምረት ለመፍጠር ወይም ሥልታዊ ስምምነቶችን ለመድረስ እየሰሩ ነው። በዚሁ ሂደት ውስጥ የፖለቲካ አቋም ወይም መርሀግብር አንዳችም ሚና አይጫወትም። »

ባዲየ ሂማ እንደታዘቡት ግን፣ የማሊ ዜጎች ካሁን ቀደም የሰሩትን ስህተት መድገም አይፈልጉም። በዚህም የተነሳ ለአሁኑ ምክር ቤታዊ ምርጫ ትልቅ ትኩረት ሰጥተዋል።

« የማሊ ዜጎች ካለፈው የፖለቲካ እና ተቋማዊ ቀውስ ትምህርት ቀስመዋል ብዬ አምናለሁ። እርግጥ፣ በምክር ቤታዊw ምርጫ ተወዳዳሪዎች ዝርዝር ውስጥ አንዳንድ ጥምረት መፈጠሩን አይተናል። ግን፣ ባለፉት ጊዚያት ያየነው ዓይነቱ ተግባብቶ የመስራቱ ፖለቲካ እንደገና አይፈጥሩም። »

Titel: DW_Soumaila-Cisse1 und 2 Schlagworte: Bamako, Präsidentschaftswahl, Spitzenkandidat, Staatsstreich, Soumaïla Cissé, URD (Union pour la République et la Démocratie, Union für Republik und Demokratie) Wer hat das Bild gemacht/Fotograf?: Katrin Gänsler Wann wurde das Bild gemacht?: 29. Juli 2013 Wo wurde das Bild aufgenommen?: Bamako, Mali

ሱማይላ ሲሴ

ለምሳሌ፣ በፕሬዚደንታዊው ምርጫ የተሸነፉት እና አሁን በምክር ቤታዊ ምርጫ በዕጩነት የቀረቡት ሱማይላ ሲሴ በምክር ቤቱ ውስጥ ጠንካራ የተቃዋሚ ወገን እንዲኖር እንደሚሰሩ አስታውቀዋል። ወጤቱ የሆነውም ቢሆን በሰሜን ማሊ ነፃ የቱዋሬግ መንግሥት ለመመሥረት የቀጠለው ውዝግብ አሳሳቢ በመሆኑ መፍትሔ ሊገኝለት ይገባል ባይ ናቸው። እርግጥ፣ ምክር ቤቱ በመፍትሔው ፍለጋ ላይ ምን ያህል ሊሰራ መቻሉ በገልፅ አልታወቀም፣ ምክንያቱም፣ ፕሬዚደንት ኢብራሂም ቡባከር ኬታ የሰሜን ማሊ ውዝግብ ድርድር በመንግሥታቸው ኃላፊነት ስር መሆኑን ነበር ያስታወቁት። እንዲያውም፣ በሰሜን ማሊ ዕርቀ ሰላም ለማውረድ እና አካባቢውን ለማልማት የሚሰራ አዲስ ሚንስቴር አቋቁመዋል። ይህ ግን ምክር ቤቱ ውዝግቡ የሚያበቃበትን እና ዕርቀ ሰላም የሚወርድበትን መንገድ ማፈላለግ አይችልም ማለት አለመሆኑን ወይዘሮ ሎማን ገልጸዋል።

« ምክር ቤቱ ለውዝግቡ ማብቃት በድርድር የሚደረስ ውጤት ሰፊ የፖለቲካ ተቀባይነት እንዲያገኝ የራሱን ድርሻ ማበርከት ይችላል። »

ዲርከ ከፕ/አርያም ተክሌ

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic