ሚያዚያ 1 ቀን እና ውሸት | ባህል | DW | 03.04.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

ሚያዚያ 1 ቀን እና ውሸት

ከትናንት ወዲያ ዕሮብ (እኢአ ሚያዚያ 1 ቀን) ፤ ምዕራባዊያን « April fools day » በማለት የሚጠሩት እና ሌሎችን ውሸት በመናገር፤ የሚያስደነግጡበት እና የሚያስጨንቁበት ዕለት ነበር። ይህ ቀን ለምን ይከበራል? የውሸት ለከቱስ የት ድረስ ነው?

የጎርጎሮሲያኑ ሚያዚያ 1 ቀንን በርካታ ኢትዮጵያውያንም ያስታውሱታል። ዕለቱ « April fools day » በማለት የሚጠራ ሲሆን ሌሎችን ውሸት በመናገር፤ ማሳሳት፣ ማስደንገጥ ብሎም ማስለቀስ ደረጃ ይደርሳሉ ።

ሰዎች ለምን (እኢአ ሚያዚያ 1 ቀን) ይዋሻሉ? የ April fools day ታሪክ ምንድን ነው? አፕሪል ፉልስ ደይ ፤ አንዳንዴ All Fools' Day ይሉታል ፤ በየትኛውም ሀገር በብሔራዊ ክብረ በዓል ደረጃ የሚከበር ዕለት አይደለም። ይሁንና ቀኑ በአውሮፓ፣ ዮናይትድ ስቴትስ፣ አውስትራሊያ፣ ካናዳ የመሣሠሉ ሀገራት የሚገኙ ሰዎች ያስቡታል። በተለይ ይህ እንደ ቀልድ ተደርጎ የውሸት ታሪክ የሚነገርበት ዕለት ከ 19ኛው ክፍለ ዘመን በኋላ እውቅና አትርፏል። ታሪኩ ባይረጋገጥም፤ አንዳንዶች ዕለቱ የታሰበው ከወቅት መቀየር ጋር ግንኙነት ስለአለው ነው ይላሉ፤ ሌሎች ደግሞ ከዘመን መቁጠሪያ ጋር የተገናኘ ነው ይላሉ።

ጥንት ሮማውያን እና ህንዳውያንን ጨምሮ ሚያዚያ 1 ቀን ነበር ዘመናቸውን የሚለውጡት። እኢአ 1582 ዓም የሮማ ካቶሊካውያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ግሪጎሪ 13ኛው ፤ አዲስ፤ «ግሪጎሪያን ካሌንደር»ተብሎ የሚጠራ እና ጁሊያንን የዘመን አቆጣጠር የሚተካ ቀመር እንዲዘጋጅ አዘዙ። በዚህም አቆጣጠር መሰረት አዲስ ዓመት ጥር 1 ቀን ይከበራል። ፈረንሳይም ይህንን አዲስ የዘመን አቆጣጠር ቀመር ተቀብላ መቁጠር ጀመረች፤ ይሁንና ይህንን ቀን በወቅቱ በርካታ ፈረንሳያውያን እንዳልተቀበሉት አልያም ደግሞ አዲስ ዓመት መግባቱን እየረሱ አዲስ ዓመትን ሚያዚያ 1 ቀን ያከብሩ እንደነበር፤ ይነገራል። በዚህም የተነሳ ሰዎች ስለ ባህሉ ስለዘመን አቆጣጠር መፋለስ እያወሱ ይቀልዱ እና ይዋሹ ጀመር፤ ስለሆነም ይህ ውሸት በመላው አውሮፓ እንደተስፋፋ እና የApril fools day መሠረቱ ይህ እንደነበር ይነገራል።። ይሁንና ታሪኩን የሚያረጋግጡ እና የተፃፉ መጽሐፍት በወቅቱ ባለመፃፋቸው ዕውነታውን ለማወቅ አዳጋች ያደርገዋል።

ያም ሆነ ይህ በዚህ ዕለት ሰዎች ሆን ብለው ይዋሻሉ፤ ይህ ኢትዮጵያም ደርሷል። የአንዳንድ ሰዎች ውሸት ከልክ ያለፈም ሲሆን ይደመጣል። በሌላኛው ሰው ላይ ምን አይነት መጥፎ ተፅህኖ ሊያሳድር እንደሚችልም ከግንዛቤ ያስገቡት አይመስልም፤

እኢአ ሚያዚያ 1 ቀን በተወሰኑ ሰዎች ዘንድ የሚታወሰውን የ« April fools day » አስመልክቶ አራት ኢትዮጵያውያን ገጠመኛቸውን አካፍለውናል።

ከድምፅ ዘገባው ያገኙታል

ልደት አበበ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic