መድረክ በደቡብ ኢትዮጵያ | ኢትዮጵያ | DW | 21.04.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

መድረክ በደቡብ ኢትዮጵያ

የመድረክ እና የሲዳማ ዞን የምርጫ ጽህፈት ቤት ዉዝግብ ተፈታ።

default

ለበርካታ ሳምንታት ሲያወዛግብ የነበረዉና እስከፍርድ ቤትም የደረሰዉ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ በአጭሩ መድረክ አዋሳና የሲዳማ ዞን ምርጫ ጽህፈት ቤት ጉዳይ ከሰሞኑ እልባት ማግኘቱ ተገልጿል። መድረክ በአዋሳ ለመወዳደር እንዲችል እጩ ለማስመዝገብ አልቻልኩም ሲል፤ የምርጫ ፅህፈት ቤቱ ደግሞ ሁለት ሰዎች ህጋዊ ደብዳቤ ይዘዉ በመቅረብ እኔ ነኝ የምመዘገብ እያሉ ችግር ፈጥረዉብኛል ይላል። አሁን መድረክ በአዋሳ እጩዎቹን እንዲያስመዘግብና እንዲወዳደር ዉሳኔ አግኝቷል።

መሳይ መኮንን

አርያም ተክሌ