መቅዲሾ-ከሃያ በላይ ሰዉ ተገደለ | ዜና | DW | 03.07.2008
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዜና

መቅዲሾ-ከሃያ በላይ ሰዉ ተገደለ

መቅዲሾ-ከሃያ በላይ ሰዉ ተገደለ

በኢትዮጵያ ጦር በሚደገፈዉ የሶማሊያ የሽግግር መንግሥት ሐይልና በደፈጣ ተዋጊዎች መካካል ትናንት በተደረገ ዉጊያ ከሃያ በለያ ሰዉ ተገደለ።የፈረሳዩ ዜና አገልግሎት አዣንስ ፍራንስ ፕረስ የአይን ምሥክሮችን ጠቅሶ እንደዘገበዉ ትናንት ማዕከላዊ ሶማሊያ ዉስጥ በኢትዮጵያ ጦርና በደፈጣ ተዋጊዎች መካካል በተደረገ ዉጊያ ሃያ ስድስት ሰዎች ተገድለዋል።ከሟቾቹ አብዛኞቹ ወታደሮች ወይም ታጣቂዎች ነበሩ።የሶማሊያ የሽግግር መንግሥትና ከአማፂዉ ቡድን አንዱ አንጃ ጅቡቲ ዉስጥ የሰላም ዉል ከተፈራረሙ ወዲሕ በርካታ ሕይወት የጠፋበት ዉጊያ ሲደረግ የትናንቱ የመጀመሪያዉ ነዉ።ይሁንና በሞቱት ሰዎች ቁጥር የዜና ምንጮች አይስማሙም።አዣንስ ፍራንስ ፕረስ አንድ ሕፃን ጨምሮ ሃያ-ስድስት ሰዉ መገደሉን ዘግቧል።አሜሪካዉ ዜና አገልግሎት አሶሽየትድ ፕረስ እንደዘገበዉ ግን የሞቱት ሰዎች ቁጥር ከሃያ አይበልጥም።የጅቡቲዉ የሰላም ዉል ተፈራራሚዎች ዉሉን ከመጪዉ ሳምንት ጀምሮ ገቢር ተስማምተዉ ነበር።ዘግይቶ በደረሰን ዘገባ መሠረት እስከ ዛሬ በቀጠለዉ ዉጊያ የሞተዉ ሰዉ ቁጥር አርባ-ሰባት ደርሷል።